Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 21:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እነ​ዚ​ያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረ​ዐ​ይት የተ​ወ​ለዱ የራ​ፋ​ይም ወገ​ኖች ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እነዚህ አራቱ በጋት የራፋይም ዘሮች የነበሩ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በሰዎቹ እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እነዚህ አራቱ በጌት የራፋይም ዘሮች የነበሩ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በአገልጋዮቹ እጅ ወደቁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እነዚህ አራቱ የጋት ኀያላን ሰዎች የራፋይም ዘሮች ሲሆኑ ሁሉንም ዳዊትና አገልጋዮቹ ገደሉአቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እነዚህም አራቱ በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፥ በዳዊትም እጅ በባሪያዎቹም እጅ ወደቀ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 21:22
11 Referências Cruzadas  

ከራ​ፋ​ይም ወገን የነ​በ​ረው ኤስቢ መጣ፤ የጦ​ሩም ሚዛን ክብ​ደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣ​ሪ​ያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊ​ት​ንም ሊገ​ድ​ለው ፈለገ።


እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ገ​ዳ​ደረ ጊዜ የዳ​ዊት ወን​ድም የሴ​ማይ ልጅ ዮና​ታን ገደ​ለው።


እነ​ዚ​ህም በጌት ውስጥ ከኀ​ያ​ላን የተ​ወ​ለዱ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱም አራት ኀያ​ላን ነበሩ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ ወደቁ።


ልጆ​ቹም ይጥፉ፤ በአ​ን​ዲት ትው​ልድ ስሙ ትጥፋ።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ሰ​ልሁ፥ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ጠቢብ በጥ​በቡ አይ​መካ፤ ኀያ​ልም በኀ​ይሉ አይ​መካ፤ ባለ​ጠ​ጋም በብ​ል​ጥ​ግ​ናው አይ​መካ፤


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


አሁን እን​ግ​ዲህ በዚያ ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን ይህን ተራ​ራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔና​ቃ​ው​ያን፥ ታላ​ላ​ቆ​ችና የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ችም በዚያ እን​ዳሉ ሰም​ተህ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረኝ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios