Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አበ​ኔ​ርም አሣ​ሄ​ልን፥ “ከም​ድር ጋር እን​ዳ​ላ​ጣ​ብ​ቅህ እኔን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ በል፤ ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ፊቴን አቅ​ንቼ አይ ዘንድ እን​ዴት ይቻ​ለ​ኛል? እን​ደ​ዚህ አይ​ሆ​ን​ምና ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ኢዮ​አብ ተመ​ለስ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እንደ ገናም አበኔር አሣሄልን፣ “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋራ ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ?” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንደገናም አበኔር፥ “እኔን ማሳደድህን ተው! እኔስ ስለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እንደገናም አበኔር “እኔን ማሳደድህን ተው! ለምን እንድገድልህ ትገፋፋኛለህ? አንተንስ ብገድል የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ማየት እችላለሁ?” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አበኔርም አሣሄልን፦ ከምድር ጋር እንዳላጣብቅህ እኔን ከማሳደዱ ፈቀቅ በል፥ ወደ ወንድምህ ወደ ኢዮአብ ፊቴን አቅንቼ አይ ዘንድ እንዴት ይቻለኛል? አለው።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 2:22
6 Referências Cruzadas  

አበ​ኔ​ርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አንድ ጐል​ማሳ ያዝ፤ መሣ​ሪ​ያ​ው​ንም ለራ​ስህ ውሰድ” አለው። አሣ​ሄል ግን እር​ሱን ከማ​ሳ​ደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።


አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።


የሆ​ነው ሁሉ እነሆ፥ ስሙ አስ​ቀ​ድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፤ ከእ​ር​ሱም ከሚ​በ​ረ​ታው ጋር ይፋ​ረድ ዘንድ አይ​ች​ልም።


ሳኦ​ልም ሜል​ኮ​ልን አላት፥ “ስለ​ምን እን​ዲህ አታ​ለ​ል​ሽኝ? ጠላ​ቴን አስ​ኰ​በ​ለ​ልሽ፤ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ጥም አደ​ረ​ግ​ሽው?” ሜል​ኮ​ልም ለሳ​ኦል፥ “እርሱ፦ አው​ጥ​ተሽ ስደ​ጂኝ፤ አለ​ዚያ እገ​ድ​ል​ሻ​ለሁ አለኝ” አለ​ችው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios