Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ዘበ​ኛ​ውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበ​ኛ​ውም ለደጅ ጠባ​ቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉ​ሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆ​ናል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አይቶ፣ ዘበኛውን ተጣራና፣ “እነሆ ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለ። ንጉሡም፣ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከዚያም ጠባቂው ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውን ተጣራና፥ “ተመልከት! ሌላም ሰው ብቻውን እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም፥ “ይኸኛውም መልካም ወሬ ይዞ የመጣ ይሆናል” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ዘበኛውም እንደገና አንድ ሌላ ሰው እየሮጠ ሲመጣ አይቶ፥ የቅጽር በር ጠባቂውን በመጣራት “ተመልከት! ሌላም አንድ ሰው እየሮጠ በመምጣት ላይ ነው!” አለው። ንጉሡም “ይህኛውም መልካም ወሬ ይዞ የሚመጣ ሊሆን ይችላል” ሲል መለሰ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እርሱም ፈጥኖ ቀረበ። ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፥ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፦ እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ አለ። ንጉሡም፦ እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል አለ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 18:26
3 Referências Cruzadas  

ዘበ​ኛ​ውም ለን​ጉሡ ሊነ​ግ​ረው ጮኸ። ንጉ​ሡም፥ “ብቻ​ውን እንደ ሆነ በአፉ ወሬ ይኖ​ራል” አለ። እር​ሱም ፈጥኖ ቀረበ።


ዘበ​ኛ​ውም፥ “የፊ​ተ​ኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪ​ማ​ሖስ ሩጫ ይመ​ስ​ላል” አለ፤ “ንጉ​ሡም፦ እርሱ መል​ካም ሰው ነው፤ መል​ካ​ምም ወሬ ያመ​ጣል” አለ።


ገብ​ተ​ውም በከ​ተ​ማው በር ጮኹ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፥ “ወደ ሶር​ያ​ው​ያን ሰፈር ገባን፤ እነ​ሆም፥ ፈረ​ሶ​ችና አህ​ዮች ታስ​ረው፥ ድን​ኳ​ኖ​ችም ተተ​ክ​ለው ነበር እንጂ ያገ​ኘ​ነው አል​ነ​በ​ረም፤ የሰ​ውም ድምፅ አል​ነ​በ​ረም።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios