Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ንጉ​ሡም ደግሞ ካህ​ኑን ሳዶ​ቅን፥ “እነሆ፥ አን​ተና ልጅህ አኪ​ማ​ኦስ፥ የአ​ብ​ያ​ታ​ርም ልጅ ዮና​ታን፥ ሁለቱ ልጆ​ቻ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር በሰ​ላም ወደ ከተማ ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እንዲሁም ንጉሡ ካህኑን ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? እንግዲህ አንተም ልጅህን አኪማአስን፣ የአብያታርን ልጅ ዮናታንን ይዘህ በሰላም ወደ ከተማዪቱ ተመለስ። አንተና አብያታር ሁለቱን ልጆቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እንዲሁም ንጉሡ ካህኑን ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? ይሄውልህ አንተም ልጅህን አሒማአስን፥ የአብያታርን ልጅ ዮናታንን ይዘህ በሰላም ወደ ከተማዪቱ ተመለስ። አንተና አብያታር ሁለቱን ልጆቻችሁን ይዛችሁ ሂዱ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ንግግሩንም በመቀጠል ሳዶቅን እንዲህ አለው፤ “ተመልከት፤ ልጅህን አሒማዓጽንና የአብያታርንም ልጅ ዮናታንን ይዘህ ወደ ከተማይቱ በሰላም ሂድ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ንጉሡም ደግሞ ካህኑን ሳዶቅን፦ እነሆ አንተና ልጅህ አኪማአስ የአብያታርም ልጅ ዮናታን ሁለቱ ልጆቻችሁ በደኅና ወደ ከተማ ተመለሱ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 15:27
11 Referências Cruzadas  

ወደ ከተማ ግን ተመ​ል​ሰህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም፦ ወን​ድ​ሞ​ችህ፥ ንጉ​ሡም መጡ። እነሆ፥ በኋ​ላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ፤ አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ባ​ትህ አገ​ል​ጋይ ነበ​ርሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ለአ​ንተ አገ​ል​ጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር ብት​ለው የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ትለ​ው​ጥ​ል​ኛ​ለህ።


እነሆ፥ የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ኦ​ስና የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን፥ ልጆ​ቻ​ቸው በዚያ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አሉ፤ የም​ት​ሰ​ሙ​ትን ሁሉ በእ​ነ​ርሱ እጅ ላኩ​ልኝ።”


ዮና​ታ​ንና አኪ​ማ​ሆ​ስም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ቆመው ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና ሄዳ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከተማ መግ​ባት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም ሄደው ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።


የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።


ዳዊ​ትም ማልዶ በተ​ነሣ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ወደ ጋድ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እር​ሱም ይህን ሲና​ገር የካ​ህኑ የአ​ብ​ያ​ታር ልጅ ዮና​ታን መጣ፤ አዶ​ን​ያ​ስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መል​ካ​ምም ታወ​ራ​ል​ና​ለ​ህና ግባ” አለው።


በን​ፍ​ታ​ሌ​ምም አኪ​ማ​ኦስ ነበረ፤ እር​ሱም የሰ​ሎ​ሞ​ንን ልጅ ባሴ​ማ​ትን አግ​ብቶ ነበር፤


እነ​ዚህ ሁሉ ቀንደ መለ​ከ​ቱን ከፍ ያደ​ርጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በን​ጉሡ ፊት የሚ​ዘ​ም​ረው የኤ​ማን ልጆች ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኤ​ማን ዐሥራ አራት ወን​ዶች ልጆ​ች​ንና ሦስት ሴቶች ልጆ​ችን ሰጠው።


አኪ​ጦ​ብም ሳዶ​ቅን ወለደ፤ ሳዶ​ቅም አኪ​ማ​ኦ​ስን ወለደ፤


ብላ​ቴ​ና​ውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በዚ​ህች ከተማ አለ፤ እር​ሱም የተ​ከ​በረ ሰው ነው፤ የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በእ​ው​ነት ይፈ​ጸ​ማል፤ አሁ​ንም ወደ​ዚያ እን​ሂድ፤ ምና​ል​ባት የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገድ ይነ​ግ​ረ​ና​ልና” አለው።


ቀድሞ ነቢ​ዩን ባለ ራእይ ይሉት ነበ​ርና አስ​ቀ​ድሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመ​ጠ​የቅ ሲሄድ፦ ኑ፤ ወደ ባለ ራእይ እን​ሂድ ይል ነበር።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios