Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 14:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ንጉ​ሡም ኢዮ​አ​ብን፥ “እነሆ፥ ይህን ነገር አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሂድና ብላ​ቴ​ና​ውን አቤ​ሴ​ሎ​ምን መል​ሰው” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ንጉሡም ኢዮአብን፣ “መልካም ነው፤ ፈቅጃለሁ፤ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ንጉሡም ኢዮአብን፥ “እነሆ፥ ፈቅጃለሁ፤ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን መልሰህ አምጣው” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ንጉሡም ዘግየት ብሎ ኢዮአብን “ተስማምቼአለሁና ሄደህ ያንን ወጣት አቤሴሎምን ፈልገህ ወደዚህ አምጣው” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ንጉሡም ኢዮአብን፦ እነሆ፥ ይህን ነገር አድርጌአለሁ፥ እንግዲህ ሂድና ብላቴናውን አቤሴሎምን መልሰው አለው።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 14:21
4 Referências Cruzadas  

ያችም ሴት፥ “ለመ​ግ​ደል ባለ ደሞች እን​ዳ​ይ​በዙ፤ ልጄ​ንም እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉ​ብኝ ንጉሥ ፈጣ​ሪው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያስብ” አለች። እር​ሱም፥ “የል​ጅ​ሽስ አን​ዲት የራሱ ጠጕር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ት​ወ​ድቅ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን” አላት።


ኢዮ​አ​ብም በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉ​ሡ​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን እን​ዳ​ገኘ አገ​ል​ጋ​ይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።


ንጉሡም እጅግ አዝኖ ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ስለ ተቀመጡት ሊነሣት አልወደደም።


እስ​ራ​ኤ​ልን የሚ​ያ​ድን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ኀጢ​ኣቱ በልጄ በዮ​ና​ታን ቢሆን ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለ። ከሕ​ዝ​ቡም ሁሉ አንድ የመ​ለ​ሰ​ለት ሰው አል​ነ​በ​ረም።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios