Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ሳሙኤል 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም በዳ​ዊት ፊት ተሰ​ል​ፈው ከእ​ርሱ ጋር ተዋጉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ መላውን እስራኤልን ሰብስቦ፤ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ኤላም ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ሁሉ በአንድነት አሰባስቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገረ፤ ከዚያም ሶርያውያን ወደ ሰፈሩበት ወደ ሔላም ሄደ፤ ሶርያውያንም በሰልፍ ወጥተው በዳዊት ላይ ጦርነት ከፈቱ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፥ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ሳሙኤል 10:17
3 Referências Cruzadas  

አድ​ር​አ​ዛ​ርም ልኮ በካ​ላ​ማቅ ወንዝ ማዶ የነ​በ​ሩ​ትን ሶር​ያ​ው​ያን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ ወደ ኤላ​ምም መጡ፤ የአ​ድ​ር​አ​ዛ​ርም ሠራ​ዊት አለቃ ሶቤቅ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።


ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት መቶ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ገደለ፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶቤ​ቅን መታ፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ።


ዳዊ​ትም በተ​ነ​ገ​ረው ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግሮ መጣ​ባ​ቸው፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ርሱ ጋር ተዋጉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios