Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ነገሥት 25:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ግን የመ​ን​ግ​ሥት ዘር የነ​በረ የኤ​ል​ሴማ ልጅ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶ​ል​ያ​ንም መታው፤ ሞተም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በመ​ሴፋ የነ​በ​ሩ​ትን አይ​ሁ​ድ​ንና ከለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ነገር ግን በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዝርያ የነበረው የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ዐሥር ሰዎች ይዞ መጥቶ ጎዶልያስንና በምጽጳ ዐብረውት የነበሩትን የይሁዳን ሰዎችና ባቢሎናውያንን ገደለ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ነገር ግን በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዘር የነበረውና የኤሊሻማዕ የልጅ ልጅ የሆነው የነታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ሄደ፤ በዚያም አደጋ ጥሎ ገዳልያን ገደለው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተገኙትን እስራኤላውያንንና ባቢሎናውያንን ሁሉ ገደለ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ነገር ግን በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ንጉሣዊ ዘር የነበረውና የኤሊሻማዕ የልጅ ልጅ የሆነው የነታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ሄደ፤ በዚያም አደጋ ጥሎ ገዳልያን ገደለው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተገኙትን እስራኤላውያንንና ባቢሎናውያንን ሁሉ ገደለ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በሰባተኛው ወር ግን የመንግሥት ዘር የነበረ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር ዐሥር ሰዎች መጥተው ጎዶልያስንና ከእርሱ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንን እስኪሞቱ ድረስ መቱአቸው።

Ver Capítulo Cópia de




2 ነገሥት 25:25
8 Referências Cruzadas  

የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


ጎዶ​ል​ያም፥ “ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሎሌ​ዎች የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ በሀ​ገሩ ተቀ​መጡ፤ ለባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ተገዙ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብሎ ለእ​ነ​ር​ሱና ለሰ​ዎ​ቻ​ቸው ማለ​ላ​ቸው።


የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ “እባ​ክህ፥ ልሂድ፤ ማንም ሳያ​ውቅ የና​ታ​ን​ያን ልጅ እስ​ማ​ኤ​ልን ልግ​ደ​ለው፤ ወደ አንተ የተ​ሰ​በ​ሰቡ አይ​ሁድ ሁሉ እን​ዲ​በ​ተኑ፥ የይ​ሁ​ዳም ቅሬታ እን​ዲ​ጠፋ ነፍ​ስ​ህን ስለ ምን ይገ​ድ​ላል?” ብሎ በመ​ሴፋ በቈ​ይታ ለጎ​ዶ​ል​ያስ ተና​ገረ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከመ​ን​ግ​ሥት ወገ​ንና ከን​ጉሡ ዋና ዋና አለ​ቆች አንዱ የኤ​ሊ​ሳማ ልጅ የና​ታ​ንያ ልጅ እስ​ማ​ኤል ከዐ​ሥር ሰዎች ጋር ወደ መሴፋ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ መጣ፤ በዚ​ያም በመ​ሴፋ በአ​ንድ ላይ እን​ጀራ በሉ።


የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሰ​ይፍ መቱ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን ገደሉ።


እስ​ማ​ኤ​ልም ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር በመ​ሴፋ የነ​በ​ሩ​ትን አይ​ሁድ ሁሉ፥ በዚ​ያም የተ​ገ​ኙ​ትን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሁሉ፤ ሰል​ፈ​ኞች ሰዎ​ች​ንም ሁሉ ገደ​ላ​ቸው።


ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios