Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ነገሥት 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፥ ባሪ​ያ​ዬም ሙሴ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሕግ ሁሉ ቢያ​ደ​ርጉ ቢጠ​ብ​ቁም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጠ​ኋት ምድር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን እግር እን​ደ​ገና አላ​ን​ቀ​ሳ​ቅ​ስም” ባለው ቤት የሠ​ራ​ውን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ው​ንም ምስል አቆመ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንዲሁም፣ “ብቻ ያዘዝኋቸውን ሁሉ ተጠንቅቀው በመፈጸምና ባሪያዬ ሙሴ የሰጣቸውንም ሕግ በሙሉ በመጠበቅ ይጽኑ እንጂ ከእንግዲህ የእስራኤላውያን እግር፣ ለአባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ምድር ወጥቶ እንዲንከራተት አላደርግም” ያለው ስለዚሁ ስፍራ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የእስራኤል ሕዝብ ትእዛዞቼን ቢጠብቁና ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትንም ሕግ ቢፈጽሙ፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ከዚህች ምድር ተነቃቅለው እንዲጠፉ አላደርግም” ሲል ነግሮአቸው የነበረው ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የእስራኤል ሕዝብ ትእዛዞቼን ቢጠብቁና ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትንም ሕግ ቢፈጽሙ፥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ከዚህች ምድር ተነቃቅለው እንዲጠፉ አላደርግም” ሲል ነግሮአቸው የነበረው ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ያዘዝኋቸውንም ሁሉ፥ ባሪያዬም ሙሴ ያዘዛቸውን ሕግ ሁሉ ቢያደርጉ ቢጠብቁም ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር የእስራኤልን እግር እንደ ገና አላቅበዘብዝም፤” ባለው ቤት የሠራውን የማምለኪያ ዐፀድን የተቀረጸውን ምስል አቆመ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ነገሥት 21:8
16 Referências Cruzadas  

ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እተ​ክ​ላ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ብቻ​ቸ​ውን ይቀ​መ​ጣሉ፤ ከዚ​ያም በኋላ የሚ​ጠ​ራ​ጠ​ሩት የለም፤ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የኀ​ጢ​አት ልጅ መከራ አያ​ጸ​ና​ባ​ቸ​ውም።


ለሕ​ዝ​ቤም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስፍራ አደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለሁ፥ በዚ​ያም እተ​ክ​ለ​ዋ​ለሁ፥ በስ​ፍ​ራ​ውም ይቀ​መ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ አይ​ና​ወ​ጥም፤ የኀ​ጢ​አ​ትም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው አያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​ትም፤


ያዘ​ዝ​ኋ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ በሙሴ የተ​ሰ​ጠ​ውን ሕግና ሥር​ዐት ፍር​ድ​ንም ሁሉ ቢያ​ደ​ርጉ ቢጠ​ብ​ቁም፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከሰ​ጠ​ኋት ምድር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን እግር እንደ ገና አላ​ር​ቅም” ባለ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የሠ​ራ​ውን ጣዖ​ትና የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል አቆመ።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


እሽ ብት​ሉና ብት​ሰ​ሙኝ የም​ድ​ርን በረ​ከት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤


ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘ​ዝ​ኋ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios