Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ነገሥት 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሕዝ​ቅ​ያ​ስ​ንም ጠሩ፤ የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነ​ርሱ ወጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ ንጉሡም ላኩበት፤ ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፣ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ፣ ታሪክ መዝጋቢውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ሄዱ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለ ሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚያም በኋላ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም ባለሟሎቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፤ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነ የሒልቂያ ልጅ ኤልያቄም፥ እንዲሁም የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሼብናና የቤተ መዛግብት ኀላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአሕ ነበሩ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ንጉሡንም ጠሩ፤ የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊውም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እነርሱ ወጡ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ነገሥት 18:18
12 Referências Cruzadas  

አዶ​ኔ​ራ​ምም ግብር አስ​ገ​ባሪ ነበረ፤ የአ​ኪ​ሎ​ትም ልጅ ኢዮ​ሳ​ፍጥ ታሪክ ጸሓፊ ነበረ፤


ጸሓ​ፊ​ዎ​ቹም የሱባ ልጆች ኤል​ያ​ብና አኪያ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሒ​ሉድ ልጅ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ነበረ።


የኬ​ል​ቅ​ዩም ልጅ ኤል​ያ​ቄም ሳም​ና​ስም ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና በሱ​ር​ስት ቋንቋ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ተና​ገር፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ቋንቋ አት​ና​ገ​ረን፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚ​ሰ​ማው ቋንቋ ለምን ትና​ገ​ራ​ለህ?” አሉት።


የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅዩ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊው ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ገቡ፥ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን የካ​ህ​ና​ቱ​ንም አለ​ቆች ማቅ ለብ​ሰው ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው።


በነ​ገ​ሠም በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ምድ​ሪ​ቱ​ንና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ካነጻ በኋላ፥ የሴ​ልያ ልጅ ሳፋን፥ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም አለቃ መዕ​ሴያ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ኢዮ​አክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ኩን ቤት ይጠ​ግኑ ዘንድ ሰደ​ዳ​ቸው።


እነሆ እና​ንተ ቀድሞ ትፈ​ሩ​አ​ቸው የነ​በሩ በግ​ር​ማ​ችሁ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የተ​ነሣ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ። መል​እ​ክ​ተ​ኞች መራራ ልቅ​ሶን እያ​ለ​ቀሱ ይላ​ካሉ፤ ሰላ​ም​ንም ይለ​ም​ናሉ።


የቤቱ አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ የሠ​ራ​ዊቱ ጸሓፊ ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ልብ​ሳ​ቸ​ውን ቀድ​ደው ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጡ፤ የራ​ፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ቃል ነገ​ሩት።


የቤ​ቱም አዛዥ የኬ​ል​ቅ​ያስ ልጅ ኤል​ያ​ቄም፥ ጸሓ​ፊ​ውም ሳም​ናስ፥ ታሪክ ጸሓ​ፊ​ውም የአ​ሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።


የቤ​ቱ​ንም አዛዥ ኤል​ያ​ቄ​ምን፥ ጸሓ​ፊ​ው​ንም ሳም​ና​ስን፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ማቅ ለብ​ሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳ​ይ​ያስ ይሄዱ ዘንድ ላካ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios