Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ነገሥት 10:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ደብ​ዳ​ቤ​ውም በደ​ረ​ሳ​ቸው ጊዜ የሀ​ገሩ ሰዎች የን​ጉ​ሡን ልጆች ሰባ​ውን ሰዎች ይዘው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም በቅ​ር​ጫት አድ​ር​ገው ወደ እርሱ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ላኩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ፣ ሰዎቹ ሰባውን ልዑላን በሙሉ ወስደው ገደሏቸው። ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ኢዩ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቁረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቊረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደ ነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ የንጉሡን ልጆች ሰባውን ሰዎች ይዘው ገደሉአቸው፤ ራሶቻቸውንም በቅርጫት አድርገው ወደ እርሱ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ነገሥት 10:7
9 Referências Cruzadas  

እነ​ዚ​ህም የአ​ው​ራ​ጃ​ዎች አለ​ቆች ጐል​ማ​ሶች ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ ሠራ​ዊ​ትም ተከ​ተ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ወጥቶ ፈረ​ሶ​ቹ​ንና ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ያዘ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል ገደ​ላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ ኢዩ፥ “ወገ​ኖ​ቼስ ከሆ​ና​ችሁ፥ ነገ​ሬ​ንም ከሰ​ማ​ችሁ የጌ​ታ​ች​ሁን ልጆች ራስ ቍረጡ፤ ነገም በዚህ ሰዓት ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወደ እኔ ይዛ​ችሁ ኑ” ብሎ ሁለ​ተኛ ደብ​ዳቤ ጻፈ​ላ​ቸው። የን​ጉ​ሡም ልጆች ሰባው ሰዎች በሚ​ያ​ሳ​ድ​ጓ​ቸው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ታላ​ላ​ቆች ዘንድ ነበሩ።


መል​እ​ክ​ተ​ኛም መጥቶ፥ “የን​ጉ​ሡን ልጆች ራስ ይዘው መጥ​ተ​ዋል” ብሎ ነገ​ረው። ንጉ​ሡም፥ “እስከ ነገ ድረስ በበሩ አደ​ባ​ባይ ሁለት ክምር አድ​ር​ጋ​ችሁ አኑ​ሩ​አ​ቸው” አለ።


በነ​ጋ​ውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌ​ታ​ዬን ቤት የወ​ነ​ጀ​ልሁ የገ​ደ​ል​ኋ​ቸ​ውም እኔ ነኝ፤ እነ​ዚ​ህ​ንስ ሁሉ የገ​ደለ ማን ነው?


የአ​ካ​ዝ​ያ​ስም እናት ጎቶ​ልያ ልጅዋ እንደ ሞተ ባየች ጊዜ ተነ​ሥታ የመ​ን​ግ​ሥ​ትን ዘር ሁሉ አጠ​ፋች።


ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios