Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ቆሮንቶስ 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ፣ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን እንዲገለጥ፥ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የኢየሱስ ሕይወት በእኛ ሰውነት እንዲገለጥ በኢየሱስ ላይ የደረሰው ሞት በእኛም ሰውነት ላይ ዘወትር ተሸክመን እንዞራለን።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን።

Ver Capítulo Cópia de




2 ቆሮንቶስ 4:10
17 Referências Cruzadas  

ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ዓለም አያ​የ​ኝም፤ እና​ንተ ግን ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እና​ን​ተም ሕያ​ዋን ትሆ​ና​ላ​ችሁ።


በሞቱ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በት​ን​ሣ​ኤው እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከሞ​ት​ንም ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ደ​ም​ን​ኖር እና​ም​ና​ለን።


መጽ​ሐፍ እን​ዳለ፥ “ስለ አንተ ዘወ​ትር ይገ​ድ​ሉ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ታ​ረዱ በጎ​ችም ሆነ​ናል።”


የክ​ር​ስ​ቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደ በዛ መጠን እን​ዲሁ መጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ ይበ​ዛ​ልና።


ሙታ​ንን በሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንጂ በራ​ሳ​ችን እን​ዳ​ን​ታ​መን በው​ስ​ጣ​ችን ለመ​ሞት ቈር​ጠን ነበር።


በድ​ካም ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልና፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀይል ሕያው ነውና፤ እኛም ከእ​ርሱ ጋር እን​ደ​ክ​ማ​ለ​ንና፤ ነገር ግን ስለ እና​ንተ በሚ​ሆን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ከእ​ርሱ ጋር በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን።


በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን።


እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ የሚ​ያ​ደ​ክ​መኝ አይ​ኑር፤ እኔ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን መከራ በሥ​ጋዬ እሸ​ከ​ማ​ለሁ።


አሁ​ንም በመ​ከ​ራዬ ደስ ይለ​ኛል፤ አካሉ ስለ ሆነች ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን፥ ከክ​ር​ስ​ቶስ መከራ ጥቂ​ቱን በሥ​ጋዬ እፈ​ጽ​ማ​ለሁ።


እንዲህ የሚለው ቃሉ የታመነ ነው “ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤


ነገር ግን ክብሩ ሲገለጥ ደግሞ ሐሤት እያደረጋችሁ ደስ እንዲላችሁ፥ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ።


ስለ ክርስቶስ ስም ብትነቀፉ የክብር መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ያርፋልና ብፁዓን ናችሁ።


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ፤ እንዲህም አለኝ “አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው እኔ ነኝ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios