Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ቆሮንቶስ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይሁን እንጂ ወንድሜን ቲቶን እዚያ ስላላገኘሁት መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ ተሰናብቻቸው ወደ መቄዶንያ ሄድሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ነገር ግን መንፈሴ ማረፍ አልቻለም፤ ምክንያቱም እዚያ ወንድሜን ቲቶን አላገኘሁትም። ስለዚህ ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን ወንድሜን ቲቶን ባለማግኘቴ መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ እዚያ ያሉትን ክርስቲያኖች ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ሄድኩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ነገር ግን ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ቆሮንቶስ 2:13
16 Referências Cruzadas  

ካሰናበታቸውም በኋላ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።


እርስ በር​ሳ​ች​ንም ተሳ​ስ​መን ተሰ​ነ​ባ​በ​ትን፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ መር​ከብ ወጣን፤ እነ​ር​ሱም ወደ ቤታ​ቸው ተመ​ለሱ።


መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።


እነሆ ቲቶን ማለ​ድ​ሁት፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ሌላ​ውን ወን​ድ​ማ​ች​ንን ላክ​ሁት፤ በውኑ ቲቶ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል አለን? በእ​ርሱ በአ​ደ​ረው መን​ፈስ የም​ን​መ​ላ​ለስ፥ እር​ሱም የሄ​ደ​በ​ትን ፍለጋ የም​ን​ከ​ተል አይ​ደ​ለ​ን​ምን?


ስለ​ዚ​ህም ተጽ​ና​ን​ተ​ናል፤ በመ​ጽ​ና​ና​ታ​ች​ንም ስለ ቲቶ ደስታ አብ​ልጦ ደስ አለን፤ በሁ​ላ​ችሁ ዘንድ ሰው​ነ​ቱን አሳ​ር​ፋ​ች​ኋ​ታ​ልና።


ስለ እና​ንተ ለእ​ርሱ በተ​መ​ካ​ሁ​በት ሁሉ አላ​ሳ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝ​ምና፤ ነገር ግን ሁሉን ለእ​ና​ንተ በእ​ው​ነት እንደ ተና​ገ​ርን፥ እን​ደ​ዚሁ ደግሞ በቲቶ ፊት ትም​ክ​ህ​ታ​ችን እው​ነት ሆነ።


በቲቶ ልብ ስለ እና​ንተ ያን መት​ጋት የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ነው።


ቲቶም ቢሆን፥ ስለ እና​ንተ አብ​ሮኝ የሚ​ሠራ ጓደ​ኛዬ ነው፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ቢሆኑ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሐዋ​ር​ያት ናቸው።


ይህ​ንም የቸ​ር​ነት ሥራ እንደ ጀመረ ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ ዘንድ ቲቶን ማለ​ድ​ነው።


ከዐ​ሥራ አራት ዓመ​ትም በኋላ ከበ​ር​ና​ባስ ጋር እንደ ገና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣሁ፤ ቲቶ​ንም ይዠው ሄድሁ።


አብ​ሮኝ የነ​በ​ረው ቲቶም አረ​ማዊ ሲሆን እን​ዲ​ገ​ዘር ግድ አላ​ል​ሁ​ትም።


ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios