Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ቆሮንቶስ 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ምክንያቱም ጌታ ራሱ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን በራሱ የሚያመሰግን ተቀባይነት አይኖረውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ፥ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሰው ለመመስገን የሚበቃው ጌታ ሲያመሰግነው ነው እንጂ ራሱን በራሱ ሲያመሰግን አይደለም።

Ver Capítulo Cópia de




2 ቆሮንቶስ 10:18
21 Referências Cruzadas  

የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ ልበ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል።


እር​ሱም፥ “እና​ን​ተስ ለሰው ይም​ሰል ትመ​ጻ​ደ​ቃ​ላ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልቡ​ና​ች​ሁን ያው​ቃል፤ በሰው ዘንድ የከ​በረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ናቀ ይሆ​ና​ልና።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ይልቅ የሰ​ውን ክብር ወደ​ዋ​ልና።


“እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እን​ደ​ም​ታ​ው​ቁት በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጁ ባደ​ረ​ገው በከ​ሃ​ሊ​ነቱ በተ​አ​ም​ራ​ቱና በድ​ንቅ ሥራ​ዎቹ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የገ​ለ​ጠ​ላ​ች​ሁን ሰው የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን ስሙ።


እን​ዲህ አድ​ርጎ ለክ​ር​ስ​ቶስ የሚ​ገዛ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝና በሰ​ውም ዘንድ የተ​መ​ረጠ ነው።


በክ​ር​ስ​ቶስ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን ኤጤ​ሌ​ንን ሰላም በሉ፤ እነ አር​ስ​ጠ​ቦ​ሎ​ስ​ንም ሰላም በሉ።


ዳሩ ግን አይ​ሁ​ዳ​ዊ​ነት በስ​ውር ነው፤ መገ​ዘ​ርም በመ​ን​ፈስ የልብ መገ​ዘር እንጂ በኦ​ሪት ሥር​ዐት አይ​ደ​ለም፤ ምስ​ጋ​ና​ውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ ከሰው አይ​ደ​ለም።


ከእ​ና​ንተ የተ​መ​ረ​ጡት ወን​ድ​ሞች ተለ​ይ​ተው እን​ዲ​ታ​ወቁ ትለ​ያዩ ዘንድ ግድ ነው።


ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ዛሬ ለምን ትመ​ረ​ም​ራ​ላ​ቸሁ? በጨ​ለማ ውስጥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያ​በራ፥ የል​ብን አሳ​ብም የሚ​ገ​ልጥ ጌታ​ችን ይመ​ጣል፤ ያን​ጊዜ ሁሉም ዋጋ​ውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቀ​በ​ላል።


እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም።


ምንም ክፉ ሥራ እን​ዳ​ት​ሠሩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ጸ​ል​ያ​ለን፤ መል​ካም ነገር እን​ድ​ታ​ደ​ርጉ ብቻ ነው እንጂ እኛ ደጎች ልን​ባል አይ​ደ​ለም፤ እኛም እንደ ተናቁ ሰዎች እን​ሆ​ና​ለን።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?


በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።


ነገር ግን በሁሉ ራሳ​ች​ንን አቅ​ን​ተን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ በብዙ ትዕ​ግ​ሥ​ትና በመ​ከራ፥ በች​ግ​ርና በጭ​ን​ቀት ሁሉ፥


የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios