Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ቆሮንቶስ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኛ መመ​ኪ​ያ​ችሁ እን​ደ​ሆን፥ እን​ዲሁ እና​ን​ተም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን መመ​ኪ​ያ​ችን እን​ድ​ት​ሆኑ በከ​ፊል እን​ዳ​ወ​ቃ​ችሁ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እናንተ በእኛ እንደምትመኩ ሁሉ እኛም በእናንተ እንደምንመካ አሁን የተረዳችሁን በከፊል ቢሆንም፣ በጌታ ኢየሱስ ቀን ሁሉን ትረዳላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እኛን በከፊል እንደተረዳችሁን፥ በጌታ ቀን እናንተ በእኛ እንደምትመኩ ሁሉ እኛም በእናንተ እንመካለን።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አሁን ስለ እኛ የምታውቁት በከፊል ነው፤ በኋላ ግን በሙላት እንደምታስተውሉት ተስፋ አደርጋለሁ፤ በዚህም ምክንያት ጌታ ኢየሱስ በሚመጣበት ቀን እኛ በእናንተ እንደምንመካ እናንተም በእኛ ትመካላችሁ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ቆሮንቶስ 1:14
16 Referências Cruzadas  

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


እር​ሱም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን ያለ ነውር ትገኙ ዘንድ እስከ ፍጻሜ ያጸ​ና​ች​ኋል።


ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በም​ት​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እን​ደ​ም​ት​ጣ​ሉና እን​ደ​ም​ት​ከ​ራ​ከሩ ሰም​ቻ​ለሁ፤ የማ​ም​ነ​ውም አለኝ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሆ​ነ​ውና በእ​ና​ንተ ላይ ባለኝ ትም​ክ​ህት ሁል​ጊዜ እገ​ደ​ላ​ለሁ።


ማንም ያሳ​ዘ​ነኝ ቢሆን፥ እኔን ብቻ ያሳ​ዘነ አይ​ደ​ለም። ከእ​ና​ንተ አንድ ሳይ​ቀር ሁላ​ች​ሁ​ንም አሳ​ዘነ እንጂ፤ አሁ​ንም ሥር​ዐት አላ​ጸ​ና​ባ​ች​ሁም።


በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።


እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ተጉ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ስለ​ዚ​ህም “የአ​ካ​ይያ ሰዎች እኮ ከአ​ምና ጀምሮ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል” ብዬ በመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ዘንድ አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ችሁ፤ እነ​ሆም የእ​ና​ንተ መፎ​ካ​ከር ብዙ​ዎ​ችን ሰዎች አት​ግ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።


የሚ​ሻ​ለ​ውን ሥራ እን​ድ​ት​መ​ረ​ም​ሩና እን​ድ​ት​ፈ​ትኑ፥ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ያለ ዕን​ቅ​ፋት ቅዱ​ሳን ትሆኑ ዘንድ፦


ዳግ​መኛ ወደ እና​ንተ በመ​ም​ጣቴ በእኔ ምክ​ን​ያት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የም​ታ​ገ​ኙት ክብር ይበ​ዛ​ላ​ችሁ ዘንድ።


እርሱ የጀ​መ​ረ​ላ​ች​ሁን በጎ​ውን ሥራ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ እርሱ እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ አም​ና​ለሁ።


የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ።


የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios