Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ፥ እጅ​ግም ብዙ ሽቱ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳ​ባም ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ ሽቱ ከቶ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም ለንጉሡ አንድ መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፣ እጅግ ብዙ ቅመማ ቅመሞችና የከበሩ ድንጋዮች ሰጠችው፤ የሳባ ንግሥት ለንጉሥ ሰሎሞን እንደ ሰጠችው ዐይነት ቅመማ ቅመም ያለ ከቶ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለንጉሡም መቶ ሀያ መክሊት ወርቅ፥ እጅግም ብዙ ሽቶ የከበረም ዕንቁ ሰጠችው፤ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ ሽቶ ከቶ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ንግሥተ ሳባ ያመጣችውን ከአራት ሺህ ኪሎ የሚበልጥ ወርቅ፥ እጅግ ብዙ ሽቶና ዕንቊ ገጸ በረከት አድርጋ ለሰሎሞን ሰጠችው፤ እርስዋ ለሰሎሞን የሰጠችው የሽቶ ዐይነት፥ ከዚያ በፊት ከቶ ታይቶ የማይታወቅ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ፥ እጅግም ብዙ ሽቱ የከበረም ዕንቍ ሰጠችው፤ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰሎሞን እንደ ሰጠችው ያለ ሽቱ ከቶ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 9:9
10 Referências Cruzadas  

አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።


ለን​ጉ​ሡም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ እጅ​ግም ብዙ ሽቶ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ ሰጠ​ችው፤ የሳባ ንግ​ሥት ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ሰጠ​ችው ያለ የሽቶ ብዛት ከዚያ ወዲያ አል​መ​ጣም ነበር።


ኪራ​ምም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ለሰ​ሎ​ሞን አመጣ።


የሳ​ባም ንግ​ሥት የሰ​ሎ​ሞ​ንን ዝና በሰ​ማች ጊዜ በግ​መ​ሎች ላይ ሽቱና ብዙ ወርቅ፥ የከ​በ​ረም ዕንቍ አስ​ጭና ከታ​ላቅ ጓዝ ጋር ሰሎ​ሞ​ንን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በእ​ን​ቆ​ቅ​ልሽ ትፈ​ት​ነው ዘንድ መጣች፤ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም በገ​ባች ጊዜ በል​ብዋ ያለ​ውን ሁሉ አጫ​ወ​ተ​ችው።


የኪ​ራም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮ​ችም ከሴ​ፌር ለሰ​ሎ​ሞን ወርቅ አመጡ፤ የሰ​ን​ደል እን​ጨ​ትና የከ​በረ ዕን​ቍም ደግሞ አመጡ።


ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ ገጸ በረ​ከ​ቱን፥ የወ​ር​ቅ​ንና የብ​ርን ዕቃ፥ ልብ​ስ​ንና የጦር መሣ​ሪ​ያን፥ ሽቱ​ው​ንም፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና በቅ​ሎ​ዎ​ችን እየ​ያዘ በየ​ዓ​መቱ ያመጣ ነበር።


በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን በዙ​ፋኑ ላይ ያስ​ቀ​ም​ጥህ ዘንድ የወ​ደ​ደህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያጸ​ና​ቸው ዘንድ ወድ​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ስለ​ዚህ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ታደ​ርግ ዘንድ በላ​ያ​ቸው አነ​ገ​ሠህ።”


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤


እን​ደ​ዚህ ብዬ ብና​ገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የል​ጆ​ች​ህን ትው​ልድ በበ​ደ​ልሁ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ፤ የሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ሙጫ፥ በዛ​ጎል ውስጥ የሚ​ገኝ ሽቱ፥ የሚ​ሸ​ት​ትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ፤ የሁ​ሉም መጠን ትክ​ክል ይሁን።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios