Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ወደ ዙፋ​ኑም የሚ​ያ​ስ​ሄዱ፥ በወ​ርቅ የተ​ለ​በጡ ስድ​ስት እር​ከ​ኖች ነበሩ፤ በዚ​ህና በዚያ በመ​ቀ​መ​ጫው አጠ​ገብ ሁለት የክ​ንድ መደ​ገ​ፊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​በት፤ በመ​ደ​ገ​ፊ​ያ​ዎ​ቹም አጠ​ገብ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዙፋኑ ባለስድስት ደረጃ ሲሆን፣ ከዙፋኑ ጋራ የተያያዘ ከወርቅ የተሠራ የእግር መርገጫ ነበረው። መቀመጫውም ግራና ቀኙ መደገፊያ ያለው ሲሆን፣ በመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመዋል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ከዙፋኑም ጋር ተጋጥመው ወደ ዙፋኑም የሚያስኬዱ ስድስት እርከኖችና የወርቅ ብርኩማ ዙፋኑ ነበረው፤ በዚህና በዚያም በመቀመጫው አጠገብ ሁለት የክንድ መደገፊያዎች ነበሩበት፥ በመደገፊያዎችም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18-19 ዙፋኑም ከታች ወደ ላይ መወጣጫ የሆኑ ስድስት ደረጃዎች ነበሩት፤ በእያንዳንዱም ደረጃ ጫፍ በግራና በቀኝ አንዳንድ የአንበሳ ምስል ሲኖር በድምሩ የተቀረጹት የአንበሳ ምስሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ ከዙፋኑ ጋር ተያይዞ ከወርቅ የተሠራ የእግር መረገጫም ነበረው፤ በሁለቱ የክንድ መደገፊያ ጫፎችም ላይ አንዳንድ የአንበሳ ምስል ነበር፤ በሌላ በየትኛውም አገር መንግሥት ይህን የመሰለ ዙፋን ከቶ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ከዙፋኑም ጋር ተጋጥመው ወደ ዙፋኑም የሚያስሄዱ ስድስት እርከኖች ነበሩ፤ የወርቅ ብርኩማም ነበረ፤ በዚህና በዚያም በመቀመጫው አጠገብ ሁለት የክንድ መደገፊያዎች ነበሩበት፤ በመደገፊያዎችም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 9:18
6 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡም ደግሞ ከዝ​ሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠራ፤ በጥሩ ወር​ቅም ለበ​ጠው።


በስ​ድ​ስ​ቱም እር​ከ​ኖች ላይ በዚ​ህና በዚያ ዐሥራ ሁለት አን​በ​ሶች ቆመው ነበር፤ በመ​ን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ እን​ዲህ ያለ ሥራ አል​ተ​ሠ​ራም።


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አን​በሳ ደቦል ያገ​ሣል፤ እንደ አን​በ​ሳም ይነ​ሣል፤ ያደ​ነ​ውን እስ​ኪ​በላ፥ የገ​ደ​ለ​ው​ንም ደሙን እስ​ኪ​ጠጣ አይ​ተ​ኛም።”


አር​ፎ​አል፥ እንደ አን​በ​ሳና እንደ አን​በሳ ደቦል ተጋ​ድ​ሞ​አል፤ ማን ያስ​ነ​ሣ​ዋል? የሚ​መ​ር​ቁህ ሁሉ የተ​መ​ረቁ ይሁኑ፤ የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህም ሁሉ የተ​ረ​ገሙ ይሁኑ።”


ከሽማግሌዎቹም አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ፥ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል፤” አለኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios