Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ሁሉ፥ የወ​ር​ቁ​ንም መሠ​ዊያ፥ ኅብ​ስተ ገጽ የነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውን ገበ​ታ​ዎች ሠራ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንደዚሁም ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆኑትን ዕቃዎች ሠራ፤ እነዚህም፦ የወርቅ መሠዊያ፣ የገጸ ኅብስቱ ጠረጴዛ፣

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሰሎሞንም በጌታ ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ የተቀደሰውንም ኅብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች ሠራ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ የሚከተሉትን ዕቃዎች ከወርቅ አሠርቶአል፦ መሠዊያውና ለእግዚአብሔር መባ ሆኖ የሚቀርበው ኅብስት ማኖሪያ ጠረጴዛ፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን ዕቃ ሁሉ፥ የወርቁንም መሠዊያ፥ የገጹንም ኅብስት የነበረባቸውን ገበታዎች፥

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 4:19
21 Referências Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤተ መዛ​ግ​ብት ከዚያ አወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ የሠ​ራ​ውን የወ​ር​ቁን ዕቃ ሁሉ ሰባ​በረ።


ዳግ​መ​ኛም ለገጹ ኅብ​ስት ገበ​ታ​ዎች ወር​ቁን በሚ​ዛን ለገ​በ​ታ​ዎቹ ሁሉ፥ ብሩ​ንም ለብሩ ገበ​ታ​ዎች እን​ደ​ዚሁ ሰጠው፤


ሰሎ​ሞ​ንም እን​ዲህ ሲል ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ላከ፥ “ከአ​ባቴ ከዳ​ዊት ጋር እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ት​ንም ቤት ይሠራ ዘንድ የዝ​ግባ እን​ጨት እንደ ላክ​ህ​ለት፥ እን​ዲሁ ለእኔ አድ​ርግ።


ዓመ​ቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ልኮ ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ደው፤ የከ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ ከእ​ርሱ ጋር አስ​ወ​ሰደ፤ የአ​ባ​ቱን የኢ​ዮ​አ​ቄ​ምን ወን​ድም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አነ​ገሠ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላ​ቁ​ንና ታና​ሹን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ የአ​ለ​ቆ​ቹ​ንም ቤት መዝ​ገብ፥ እነ​ዚ​ህን ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን ወሰደ።


ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ ገበ​ታ​ዎች ሠርቶ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው። አንድ መቶም የወ​ርቅ ጽዋ​ዎ​ችን ሠራ።


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከዚች ስፍራ ወደ ባቢ​ሎን የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ዕቃ​ዎች ሁሉ በሁ​ለት ዓመት ውስጥ ወደ​ዚ​ህች ስፍራ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤


ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።


ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ካለ በወርቅ ከተሠራ መሠዊያ ቀንዶች አንድ ድምፅ ሰማሁ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios