Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በቤ​ቱም ፊት የነ​በ​ረው ወለል ርዝ​መቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስ​ጡ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በቤተ መቅደሱ አዳራሽ ፊት ለፊት ያለው በረንዳ ርዝመቱ በቤተ መቅደሱ ወርድ ልክ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ከፍታውም ሃያ ክንድ ነበር። ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሀያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በመግቢያው በር ያለው በረንዳም ቁመቱ ኀምሳ አራት ሜትር ሲሆን፥ ወርዱ ልክ እንደ ቤተ መቅደሱ ወርድ ዘጠኝ ሜትር ነው፤ ውስጡም በንጹሕ ወርቅ እንዲለበጥ አደረገ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በቤቱም ፊት የነበረው ወለል ርዝመቱ እንደ ቤቱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም መቶ ሃያ ክንድ ነበረ፤ ውስጡንም በጥሩ ወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 3:4
6 Referências Cruzadas  

በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ መቅ​ደሱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ከቤቱ ወደ ፊት ዐሥር ክንድ ነበረ፤ ቤቱ​ንም ሠርቶ ጨረሰ።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ያነጹ ጀመር፤ በዚ​ያ​ውም ወር በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወለል ደረሱ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በስ​ም​ንት ቀን አነጹ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ስድ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈጸሙ።


ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመ​ጣኝ፤ የደጀ ሰላ​ሙ​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፤ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም በዚህ ወገ​ንና በዚያ ወገን የነ​በ​ሩት ግን​ቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ በሰ​ሎ​ሞን ደጅ መመ​ላ​ለሻ ይመ​ላ​ለስ ነበር።


ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ይዘ​ውት ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደን​ግ​ጠው ወደ ሰሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ ወደ እነ​ርሱ ሮጡ።


በሐ​ዋ​ር​ያት እጅም በሕ​ዝቡ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ​ዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም በሰ​ሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ በአ​ን​ድ​ነት ነበሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios