Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 25:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አሜ​ስ​ያ​ስም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍራ የሰ​ጠ​ሁት መቶ መክ​ሊት ምን ይሁን?” አለው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው፥ “ከዚህ አብ​ልጦ ይሰ​ጥህ ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሳ​ነ​ውም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው፣ “ታዲያ ለእነዚህ ለእስራኤል ወታደሮች የከፈልሁት መቶ መክሊት እንዴት ይሁን?” ሲል ጠየቀው። የእግዚአብሔርም ሰው፣ “እግዚአብሔር ከዚህ አብልጦ ሊሰጥህ ይችላል” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሠራዊት የሰጠሁት መቶ መክሊት ምን ይሆን?” የጌታም ሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “ጌታ ከዚህ አብልጦ ሊሰጥህ ይችላል።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አሜስያስ፥ ነቢዩን “አስቀድሜ የከፈልኩትስ ያ ሁሉ ገንዘብ እንዴት ሊሆን ነው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “እግዚአብሔር ከዚህ ገንዘብ ይበልጥ የበዛ ሊሰጥህ ይችላል!” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው “ለእስራኤል ጭፍራ የሰጠሁት መቶ መክሊት ምን ይሁን?” አለው። የእግዚአብሔርም ሰው “ከዚህ አብልጦ ይሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ይችላል” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 25:9
4 Referências Cruzadas  

ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም ከኤ​ፍ​ሬም ከተ​ሞች የመጡ ጭፍ​ሮች ወደ ስፍ​ራ​ቸው ይመ​ለሱ ዘንድ ለይቶ አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ስለ​ዚ​ህም ቍጣ​ቸው በይ​ሁዳ ላይ ጸና፤ ወደ ስፍ​ራ​ቸ​ውም በጽኑ ቍጣ ተመ​ለሱ።


አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ነፍ​ሴን አነ​ሣ​ለሁ።


የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።


ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios