Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 25:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች በል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ችም በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፋንታ አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ግን አል​ገ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈው ሕግ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢአቱ ይሙት እንጂ ወላጆች በልጆቻቸው አይገደሉ፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ብሎ ባዘዘው መሠረት አደረገ እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አሜስያስ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም ነበር ምክንያቱም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ፥ ጌታ እንዲህ ብሎ አዝዞ ነበርና፦ “ሰው ሁሉ በገዛ ኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች ፋንታ አይሙቱ፥ ልጆችም በአባቶች ፋንታ አይሙቱ።”

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ልጆቻቸውንም ያልገደለበት ምክንያት እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ሕግ “ወላጆች ልጆቻቸው በፈጸሙት ወንጀል፥ ልጆችም ወላጆቻቸው በፈጸሙት ወንጀል በሞት አይቀጡም፤ አንድ ሰው በሞት መቀጣት ያለበት ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ ነው” ሲል የተናገረውን ቃል በማክበር ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም “ሰው ሁሉ በገዛ ኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች ፋንታ አይሙቱ፤ ልጆችም በአባቶች ፋንታ አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮችን ልጆች አልገደለም።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 25:4
6 Referências Cruzadas  

ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ ሰበ​ሰበ፤ እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አቆ​ማ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁሉ የሽህ አለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ችን አደ​ረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰ​ል​ፍም የሚ​ወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚ​ይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎ​ችን አገኘ።


ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።


እነሆ ነፍ​ሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአ​ባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እን​ዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢ​አት የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች።


“አባ​ቶች ስለ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው አይ​ገ​ደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ በኀ​ጢ​አቱ ይገ​ደል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios