Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 24:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሠራ​ተ​ኞ​ችም ሠሩ፤ ሥራ​ውም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተፈ​ጸመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት እንደ ቀድ​ሞው ሥራ መለሱ፤ አጽ​ን​ተ​ውም አቆ​ሙት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በሥራው ላይ የተሰማሩት ሰዎች ትጉሃን ስለ ነበሩ፣ ሥራው በእጃቸው ተከናወነ፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ቀደም ሲል በነበረው ዐይነት ዐደሱት፤ አጠናከሩትም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሠራተኞችም ሠሩ፥ የፈረሰውም በእጃቸው ተጠገነ፤ የጌታንም ቤት ቀድሞ ወደ ነበረበት ሁኔታ መለሱት፥ አጽንተውም አቆሙት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሠራተኞቹም በብርቱ ትጋት በመሥራት ቤተ መቅደሱን ቀድሞ በነበረው ሁኔታ በጥሩ አኳኋን አደሱት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሠራተኞችም ሠሩ፤ የፈረሰውም በእጃቸው ተጠገነ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት እንደ ቀድሞው ሥራ መለሱ፤ አጽንተውም አቆሙት።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 24:13
7 Referências Cruzadas  

ዳዊ​ትም፥ “ልጄ ሰሎ​ሞን ታና​ሽና ለጋ ብላ​ቴና ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሠ​ራው ቤት እጅግ ማለ​ፊ​ያና በሀ​ገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እን​ዲ​ጠራ ይሆን ዘንድ ይገ​ባል፤ ስለ​ዚህ አዘ​ጋ​ጅ​ለ​ታ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም ሳይ​ሞት አስ​ቀ​ድሞ ብዙ አዘ​ጋጀ።


ንጉ​ሡና ኢዮ​አ​ዳም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሥራ ላይ ለተ​ሾ​ሙት ሰጡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የሚ​ጠ​ግ​ኑ​ትን ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና አና​ጢ​ዎ​ችን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት የሚ​ያ​ድ​ሱ​ትን የብ​ረ​ትና የናስ ሠራ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​ጥ​ሩ​በት ነበር።


በጨ​ረ​ሱም ጊዜ የተ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘብ ወደ ንጉ​ሡና ወደ ካህኑ ኢዮ​አዳ ፊት አመጡ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃ፥ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ትና ለቍ​ር​ባን ዕቃ፥ ለጭ​ል​ፋ​ዎ​ችም፥ ለወ​ር​ቅና ለብ​ርም ዕቃ አደ​ረ​ጉት። በኢ​ዮ​አ​ዳም ዘመን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሁል​ጊዜ ያቀ​ርቡ ነበር።


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሚ​ሠ​ሩት የመ​ቅ​ደ​ሱን ሥራ የሚ​ሠሩ ጠቢ​ባን ሁሉ መጡ፤


በቀድሞ ክብሩ ሳለ ይህን ቤት ያየ በእናንተ መካከል የቀረ ማን ነው? ዛሬስ እንዴት ሆኖ አያችሁት? በዓይናችሁ እንደ ምናምን አይደለምን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios