Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 23:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻ​ፈው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በደ​ስ​ታና በመ​ዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የከ​ፈ​ላ​ቸ​ውን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ሾመ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈውና ዳዊትም እንዳዘዘው፣ በደስታና በመዝሙር የሚቃጠለውን የእግዚአብሔርን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት ለመደባቸው ካህናትና ሌዋውያን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ኀላፊነት ሰጣቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው፥ እንደ ዳዊትም ትእዛዝ፥ በደስታና በመዝሙር ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ዳዊት በጌታ ቤት የከፈላቸውን ካህናትና ሌዋውያን በጌታ ቤት አገልግሎት ላይ ሾመ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ዮዳሄ ካህናቱንና ሌዋውያኑን የቤተ መቅደሱ ሥራ ኀላፊዎች እንዲሆኑ አደረገ፤ የእነርሱም ተግባር በንጉሥ ዳዊት የተመደበላቸውን ሥራ ማከናወንና በኦሪት ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን መሥዋዕት ማቃጠል ነበር፤ እንዲሁም በዳዊት መመሪያ መሠረት የዜማና የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ኀላፊነት ተሰጥቶአቸው ነበር፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዮዳሄም በሙሴ ሕግ እንደተጻፈው፥ እንደ ዳዊትም ትእዛዝ፥ በደስታና በመዝሙር ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት የከፈላቸውን ካህናትና ሌዋውያን በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ላይ ሾመ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 23:18
13 Referências Cruzadas  

ዳዊ​ትም እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ዕረ​ፍት ሰጥ​ቶ​አል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይቀ​መ​ጣል።


ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ አሳ​ርጉ” አለ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት ማሳ​ረግ በተ​ጀ​መረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዝ​ሙር ደግሞ ተጀ​መረ፤ መለ​ከ​ቱም ተነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ የዳ​ዊት ዜማ ዕቃ ተመታ።


ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና አለ​ቆ​ቹም በዳ​ዊ​ትና በነ​ቢዩ በአ​ሳፍ ቃል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ ሌዋ​ው​ያ​ንን አዘዙ። በደ​ስ​ታም አመ​ሰ​ገኑ፤ አጐ​ነ​በ​ሱም፤ ሰገ​ዱም።


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተነ​ሥ​ተው ሕዝ​ቡን ባረኩ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም ተሰማ፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ውም ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያው ወደ ሰማይ ዐረገ።


ካህ​ና​ቱ​ንም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው አቆመ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ አጸ​ና​ቸው።


የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አወጡ፤ ታቦ​ቷ​ንም ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያኑ አወጡ።


ካህ​ና​ቱም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ኑም ደግሞ፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ለ​ውን የዳ​ዊ​ትን መዝ​ሙር እየ​ዘ​መሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህ​ና​ቱም በፊ​ታ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ቆመው ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት እጃ​ቸ​ውን ያጸና ዘንድ የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ልብ ወደ እነ​ርሱ መል​ሶ​አ​ልና የቂ​ጣ​ውን በዓል ሰባት ቀን በደ​ስታ አደ​ረጉ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios