Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 22:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም አካዝያስን ለመፈለግ ሄደ፤ የእርሱም ሰዎች አካዝያስን በሰማርያ ከተደበቀበት አግኝተው ያዙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት። “እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው” በማለት ቀበሩት። ስለዚህ ከአካዝያስ ቤት የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዝ ዘንድ የሚችል ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አካዝያስንም ፈልገው፥ በሰማርያም ተሸሽጎ ሳለ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት እንዲህም ብለው ቀበሩት፦ “በፍጹም ልብ ጌታን የፈለገው የኢዮሣፍጥ ልጅ ነው።” ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥቱን ለመግዛት የሚችል አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አካዝያስንም ፈልገው በሰማርያ ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አምጥተው ገደሉት፤ ነገር ግን የተቻለውን ያኽል እግዚአብሔርን ያገለግል ስለ ነበረው ስለ አያቱ ስለ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ሲሉ ሬሳውን ቀበሩት። ከአካዝያስ ቤተሰብ አባላት መካከል መንግሥቱን ሊመራ የሚችል አንድም ሰው አልተረፈም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አካዝያስንም ፈልገው፤ በሰማርያም ተሸሽጎ ሳለ አገኙት፤ ወደኢዩም አምጥተው ገደሉትና “በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን የፈለገው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበሩት። ከአካዝያስም ቤት ማንም መንግሥትን ይይዝ ዘንድ የሚችል አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 22:9
14 Referências Cruzadas  

ከይ​ሁ​ዳም የመ​ጣ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ላይ አም​ፀ​ሃ​ልና፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዘ​ዘ​ህን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቅ​ህ​ምና፥


ደን​ገ​ጡ​ሮ​ች​ሽም ሊቀ​በ​ሉሽ ይወ​ጣሉ፤ ልጅ​ሽም ሞተ ይሉ​ሻል፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ይቀ​ብ​ሩ​ት​ማል፤ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት በዚህ ልጅ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​በ​ታ​ልና ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም እርሱ ብቻ ይቀ​በ​ራል።


ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም፥ ከዝ​ያም በኋላ፥ “ሂዱ፥ ይህ​ችን የተ​ረ​ገ​መች እዩ​አት፤ የን​ጉሥ ልጅ ናትና ቅበ​ሩ​አት” አለ።


ነገር ግን የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችን ከም​ድረ ይሁዳ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትፈ​ልግ ዘንድ ልብ​ህን አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ሃ​ልና መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​ብ​ሃል” አለው።


ወደ ይሁ​ዳም ወጡ፤ በረ​ቱ​ባ​ቸ​ውም፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንም፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም ወሰዱ፤ ከታ​ና​ሹም ልጅ ከአ​ካ​ዝ​ያስ በቀር ልጅ አል​ቀ​ረ​ለ​ትም።


መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያ​ዝ​ን​ለት ሄደ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ እንጂ በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።


ኢዩም የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ይበ​ቀል ዘንድ የይ​ሁ​ዳን መሳ​ፍ​ን​ትና አካ​ዝ​ያ​ስን ያገ​ለ​ግሉ የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ካ​ዝ​ያ​ስን ወን​ድ​ሞች አግ​ኝቶ ገደ​ላ​ቸው።


ከእ​ር​ሱም ዘንድ አል​ፈው ከሄዱ በኋላ እጅግ ታሞ ሳለ ተዉት፤ የገዛ ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ስለ ካህኑ ስለ ኢዮ​አዳ ልጅ ደም ተበ​ቅ​ለው በአ​ል​ጋው ላይ ገደ​ሉት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ነገር ግን በነ​ገ​ሥ​ታት መቃ​ብር አል​ቀ​በ​ሩ​ትም።


አሜ​ስ​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል በራቀ ጊዜ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የዐ​መፅ መሐላ አደ​ረ​ጉ​በት፤ ወደ ለኪ​ሶም ኮበ​ለለ፤ በስ​ተ​ኋ​ላ​ውም ወደ ለኪሶ ላኩ፤ በዚ​ያም ገደ​ሉት።


አን​ተ​ንም እማ​ል​ዳ​ለሁ፤ እለ​ም​ን​ህ​ማ​ለሁ፤ ይቅር በለኝ፤ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ ለኀ​ጢ​አ​ቴም አሳ​ል​ፈህ አት​ስ​ጠኝ።


እና​ንተ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ በፍ​ጹም ልባ​ች​ሁም ከሻ​ች​ሁኝ ታገ​ኙ​ኛ​ላ​ችሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios