Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 21:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ከነ​ቢ​ዩም ከኤ​ል​ያስ እን​ዲህ የሚል ጽሕ​ፈት መጣ​በት፥ “የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በአ​ባ​ትህ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ መን​ገድ፥ በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ መን​ገድ አል​ሄ​ድ​ህ​ምና፥

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከነቢዩ ከኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለኢዮራም መጣ፤ “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘አንተ በአባትህ በኢዮሣፍጥ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህም፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ መጣለት፦ “የአባትህ የዳዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ነቢዩ ኤልያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ለኢዮራም ላከ፦ “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአባትህን የንጉሥ ኢዮሣፍጥን ወይም የአያትህን የንጉሥ አሳን መልካም ምሳሌነት አልተከተልክም፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ጽሕፈት መጣበት “የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ‘በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፤

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 21:12
14 Referências Cruzadas  

አሳም እንደ አባቱ እንደ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


በአ​ባ​ቱም በአሳ መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ፈቀቅ አላ​ለም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን አደ​ረገ፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችን አላ​ራ​ቀም፤ ሕዝ​ቡም ገና በኮ​ረ​ብ​ቶቹ ላይ ባሉት መስ​ገ​ጃ​ዎች ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኤል​ያ​ስን በዐ​ውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ በሚ​ያ​ወ​ጣው ጊዜ ኤል​ያ​ስና ኤል​ሳዕ ከጌ​ል​ጌላ ተነ​ሥ​ተው ሄዱ።


ሁለ​ቱም እየ​ተ​ነ​ጋ​ገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእ​ሳት ሰረ​ገ​ላና የእ​ሳት ፈረ​ሶች በሁ​ለቱ መካ​ከል ገብ​ተው ከፈ​ሉ​አ​ቸው፤ ኤል​ያ​ስም በዐ​ውሎ ነፋስ ንው​ጽ​ው​ጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።


አብ​ያም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሳ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ። በእ​ር​ሱም ዘመን ምድ​ሪቱ ዐሥር ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


“አንድ የመ​ጽ​ሐፍ ክር​ታስ ውሰድ፥ ለአ​ን​ተም ከተ​ና​ገ​ር​ሁ​በት ቀን ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ጻፍ​በት።


ይሁ​ዳም ሦስ​ትና አራት ዐምድ ያህል በአ​ነ​በበ ቍጥር፥ ንጉሡ በብ​ርዕ መቍ​ረጫ ቀደ​ደው፤ ክር​ታ​ሱ​ንም በም​ድጃ ውስጥ በአ​ለው እሳት ፈጽሞ እስ​ኪ​ቃ​ጠል ድረስ በም​ድጃ ውስጥ ወደ አለው እሳት ጣለው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios