Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 14:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለአ​ሳም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚ​ሸ​ከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይ​ሁዳ ሠራ​ዊት፥ ወን​ጭፍ የሚ​ወ​ነ​ጭፉ፥ ቀስ​ትም የሚ​ገ​ትሩ ሁለት መቶ ሰማ​ንያ ሺህ የብ​ን​ያም ሰዎች ነበ​ሩት፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የያዙ ሦስት መቶ ሺሕ የይሁዳ ሰዎች እንዲሁም ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማንያ ሺሕ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት፥ ጋሻም የሚሸከሙ ቀስትም የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ንጉሥ አሳ ታላላቅ ጋሻና ጦር የታጠቁ ሦስት መቶ ሺህ ሠራዊት ከይሁዳ፥ ታናናሽ ጋሻና ቀስት የያዙ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ ሠራዊት ከብንያም ነበሩት፤ እነዚህ ሁሉ በሚገባ የሠለጠኑ ጀግኖች ወታደሮች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለአሳም አላባሽ አግሬ ጋሻና ጦር የሚሸከሙ ሦስት መቶ ሺህ የይሁዳ ሠራዊት እና ጋሻ የሚሸከሙ፥ ቀስት የሚገትሩ ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ የብንያም ሰዎች ነበሩት፤ እነዚህም ሁሉ ጽኑዓን ኃያላን ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 14:8
11 Referências Cruzadas  

ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ከጥ​ፍ​ጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ አሠራ፤ በአ​ን​ዱም አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ ውስጥ የገ​ባው ወርቅ ሦስት መቶ ሰቅል ነበረ።


የኡ​ላም ልጆች ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ንና ቀስ​ተ​ኞች ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም መቶ አምሳ የሚ​ያ​ህሉ ብዙ ልጆ​ችና የልጅ ልጆች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ዚህ ሁሉ የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


ሮብ​ዓ​ምም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በመጣ ጊዜ እስ​ራ​ኤ​ልን ወግ​ተው መን​ግ​ሥ​ቱን ወደ ሮብ​ዓም ይመ​ልሱ ዘንድ ከይ​ሁ​ዳና ከብ​ን​ያም ቤት የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አንድ መቶ ሰማ​ንያ ሺህ ሰል​ፈ​ኞች ጐል​ማ​ሶ​ችን ሰበ​ሰበ።


ጌትን፥ መሪ​ሳን፥ ዚፍን፥


ሮብ​ዓም በነ​ገሠ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የግ​ብፅ ንጉሥ ሱስ​ቀም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ለ​ዋ​ልና፤


ሺህ ሁለት መቶ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ስድሳ ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይዞ መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከግ​ብፅ ለመ​ጣው ሕዝብ ቍጥር አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ እነ​ር​ሱም የል​ብያ ሰዎች፥ ሞጠ​ግ​ሊ​ያ​ና​ው​ያን፥ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሰዎች ነበሩ።


አብ​ያም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን አራት መቶ ሺህ ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞች ይዞ ወደ ሰልፍ ወጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም የተ​መ​ረ​ጡ​ትን ስም​ንት መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ይዞ በእ​ርሱ ላይ ተሰ​ለፈ።


ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ በኋላ የሞ​ዓ​ብና የአ​ሞን ልጆች ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ምዑ​ና​ው​ያን ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ሊወጉ መጡ።


ንጉሡ አሜ​ስ​ያ​ስም የይ​ሁ​ዳን ሕዝብ ሰበ​ሰበ፤ እንደ እየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አቆ​ማ​ቸው፤ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሁሉ የሽህ አለ​ቆ​ች​ንና የመቶ አለ​ቆ​ችን አደ​ረገ፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ሁሉ ቈጠረ፤ ለሰ​ል​ፍም የሚ​ወጡ፥ ጋሻና ጦርም የሚ​ይዙ ሦስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎ​ችን አገኘ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios