Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊ​ታ​ቸ​ውና በኋ​ላ​ቸው ነበረ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኹ፤ ካህ​ና​ቱም መለ​ከ​ቱን ነፉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የይሁዳም ሰዎች ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከፊትና ከኋላ መከበባቸውን አዩ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከታቸውን ነፉ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ይሁዳም ወደ ኋላው በተመለከተ ጊዜ፥ እነሆ፥ ጦርነቱ በፊቱና በኋላው ነበረ፤ ወደ ጌታም ጮኹ፥ ካህናቱም መለከቱን ነፉ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የይሁዳ ሕዝብም ዙሪያውን ተመልክቶ መከበቡን ባየ ጊዜ እንዲረዳው ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ካህናቱም እምቢልታ ነፉ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ይሁዳም ወደ ኋላው በተመለከተ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊቱና በኋላው ነበረ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቱን ነፉ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 13:14
12 Referências Cruzadas  

በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።


አሳም፥ “አቤቱ፥ በብ​ዙም ሆነ በጥ​ቂቱ ማዳን አይ​ሳ​ን​ህም፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ በአ​ንተ ታም​ነ​ና​ልና፥ በስ​ም​ህም በዚህ ታላቅ ወገን ላይ መጥ​ተ​ና​ልና ርዳን፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን አንተ ነህ፤ ሰውም አያ​ሸ​ን​ፍ​ህም” ብሎ ወደ አም​ላኩ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


ንጉሡ ሕዝ​ቅ​ያ​ስና የአ​ሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳ​ይ​ያስ ስለ​ዚህ ተግ​ዳ​ሮት ጸለዩ፤ ወደ ሰማ​ይም ጮኹ።


አቤቱ፥ ከን​ፈ​ሮ​ችን ክፈት፥ አፌም ምስ​ጋ​ና​ህን ያወ​ራል።


አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥ አሳ​ብ​ህም እጅግ ጥልቅ ነው።


ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።


በሚ​ገ​ፋ​ች​ሁም ጠላት ላይ በም​ድ​ራ​ችሁ ወደ ሰልፍ ስት​ወጡ በም​ል​ክት መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ትታ​ሰ​ባ​ላ​ችሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ትድ​ና​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ በዞ​ሩና ካህ​ናቱ ቀንደ መለ​ከ​ቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና ጩኹ።


የጋ​ይም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው ዞረው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወዲ​ህና ወዲያ መሸሽ አል​ቻ​ሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው ላይ ተመ​ለሱ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios