Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 12:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተመ​ለ​ሱና እንደ ተፀ​ፀቱ ባየ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ “ከተ​መ​ለሱ አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ከጥ​ቂት ቀንም በኋላ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቍጣ​ዬም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ አይ​ፈ​ስ​ስም” ሲል ወደ ሰማያ መጣ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያ መጣ፤ “ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ስላዋረዱ እታደጋቸዋለሁ እንጂ አላጠፋቸውም፤ ቍጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የጌታ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሸማያ መጣ፦ “ራሳቸውን አዋርደዋል፤ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፥ ቁጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይወርድም፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ፥ ነቢዩ ሸማዕያን እንደገና እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ በደላቸውን አምነው ራሳቸውን ስላዋረዱ፥ አላጠፋቸውም፤ ሺሻቅ አደጋ በሚጥልባቸው ጊዜ፥ ፈጥኜ በመታደግ አድናቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ቊጣዬን ሙሉ በሙሉ አላወርድም፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም ሰውነታቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል” ሰውነታቸውን አዋርደዋል፤ አላጠፋቸውም፤ ከጥቂት ቀንም በኋላ አድናቸዋለሁ፤ ቍጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም፤

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 12:7
21 Referências Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ራራ​ላ​ቸው፤ ማራ​ቸ​ውም፤ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን እነ​ር​ሱን ተመ​ለ​ከተ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም፤ ፈጽ​ሞም ከፊቱ አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም።


በተ​ፀ​ፀ​ተም ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ከእ​ርሱ ዘንድ ራቀ፤ ፈጽ​ሞም አላ​ጠ​ፋ​ውም፤ በይ​ሁዳ መል​ካም ነገር ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰው​ነ​ቱን አዋ​ረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ቍጣ​ውን አላ​መ​ጣ​ባ​ቸ​ውም።


በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።


የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ልጅ ምና​ሴም ጸለየ እን​ዲ​ህም አለ፦


“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ አባ​ቶ​ቻ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ጠ​በቁ፥ በላ​ያ​ችን የነ​ደደ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ እጅግ ነውና ሄዳ​ችሁ ስለ ተገ​ኘው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ስለ​እኔ፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ስለ​ቀ​ሩ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቁ” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


በእ​ጃ​ቸው ሥራ ሁሉ ሊያ​ስ​ቈ​ጡኝ ትተ​ው​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት አጥ​ነ​ዋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


በፊ​ቴም ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ በዚ​ህም ስፍራ በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ ቃሌን በሰ​ማህ ጊዜ ራስ​ህን አዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህ​ንም ቀድ​ደህ በፊቴ አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ችን መነ​ጋ​ገ​ሪያ አደ​ረ​ግ​ኸን፥ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንም በላ​ያ​ችን ተሳ​ለ​ቁ​ብን።


ስለ​ዚህ የቍ​ጣ​ውን መዓ​ትና የሰ​ል​ፉን ጽናት አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸው አቃ​ጠ​ላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ እን​ዳ​መ​ፅሽ፥ መን​ገ​ድ​ሽ​ንም ከለ​መ​ለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእ​ን​ግ​ዶች እንደ ዘረ​ጋሽ፥ ቃሌ​ንም እን​ዳ​ል​ሰ​ማሽ ኀጢ​አ​ት​ሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እን​ግ​ዲህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣ​ዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎ​ችና በም​ድር ፍሬ ላይ ይፈ​ስ​ሳል፤ ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋ​ምም።”


እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios