Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት እን​ዳ​ይ​ሆኑ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ልጆቹ አስ​ለ​ቅ​ቀ​ዋ​ቸው ነበ​ርና ሌዋ​ው​ያን መሰ​ም​ሪ​ያ​ቸ​ውን ትተው ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኢዮርብዓምና ልጆቹ ሌዋውያኑን ከእግዚአብሔር የክህነት አገልግሎት ስላባረሯቸው ሌዋውያኑ ማሰማሪያ ቦታቸውንና ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጌታም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓምና በእርሱ እግር የተተኩት ዘሮቹ ሌዋውያንን የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ስላልፈቀዱላቸው ሌዋውያን ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የግጦሽ ቦታዎቻቸውንና የቀረውንም ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔርም ካህናት እንዳይሆኑ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያን መሰማርያቸውንና ቦታቸውን ትተው ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 11:14
10 Referências Cruzadas  

ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከክ​ፋቱ አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች አብ​ልጦ ከሕ​ዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​ድስ ነበር፤ እር​ሱም ለኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህን ይሆን ነበር።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ዘንድ የነ​በሩ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ሁሉ ወደ እርሱ መጡ።


የአ​ሮ​ንን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን አላ​ሳ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ምን? ከም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ለራ​ሳ​ችሁ ካህ​ና​ትን አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምን? አንድ ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎ​ችን ይዞ ራሱን ይቀ​ድስ ዘንድ የሚ​መጣ ሁሉ አማ​ል​ክት ላል​ሆ​ኑት ለእ​ነ​ዚያ ካህን ይሆ​ናል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios