Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




2 ዜና መዋዕል 10:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ንጉ​ሡም ጽኑ ምላሽ መለ​ሰ​ላ​ቸው፤ ንጉ​ሡም ሮብ​ዓም የሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን ምክር ትቶ፦

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ንጉሡ ሮብዓምም በሽማግሌዎቹ የተሰጠውን ምክር ንቆ ሕዝቡን የሚያስከፋ መልስ ሰጣቸው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ንጉሡም ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ትቶ፦

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ንጉሥ ሮብዓምም ሽማግሌዎቹ የሰጡትን ምክር ውድቅ አድርጎ ሕዝቡን በማመናጨቅ መናገር ጀመረ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ንጉሡም ጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎቹን ምክር ትቶ

Ver Capítulo Cópia de




2 ዜና መዋዕል 10:13
11 Referências Cruzadas  

“የሀ​ገሩ ጌታ የሆ​ነው ሰው በክፉ ንግ​ግር ተና​ገ​ረን፤ የም​ድ​ሪ​ቱም ሰላ​ዮች እን​ደ​ሆን አድ​ርጎ ወደ እስር ቤት አስ​ገ​ባን።”


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን በአ​ያ​ቸው ጊዜ ዐወ​ቃ​ቸው፤ እን​ደ​ማ​ያ​ው​ቃ​ቸ​ውም ሆነ፤ ክፉ ቃል​ንም ተና​ገ​ራ​ቸው፥ “እና​ንተ ከወ​ዴት መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ከከ​ነ​ዓን ምድር እህል ልን​ሸ​ምት የመ​ጣን ነን” አሉት።


ንጉ​ሡም፥ “በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ እኔ ተመ​ለሱ” ብሎ እንደ ተና​ገረ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምና ሕዝቡ ሁሉ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ወደ ሮብ​ዓም መጡ።


“አባቴ ቀን​በር አክ​ብ​ዶ​ባ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን እጨ​ም​ር​በ​ታ​ለሁ፤ አባቴ በአ​ለ​ንጋ ገር​ፎ​አ​ችሁ ነበር፤ እኔ ግን በጊ​ንጥ እገ​ር​ፋ​ች​ኋ​ለሁ” ብሎ እንደ ብላ​ቴ​ኖቹ ምክር ተና​ገ​ራ​ቸው።


እርሱ ግን ሽማ​ግ​ሌ​ዎች የመ​ከ​ሩ​ትን ነገር ትቶ ከእ​ርሱ ጋር ካደ​ጉ​ትና በፊቱ ይቆሙ ከነ​በ​ሩት ብላ​ቴ​ኖች ጋር ተማ​ከረ።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በም​ት​ታ​ይ​በት ቀን ትሞ​ታ​ለ​ህና ዳግ​መኛ ፊቴን እን​ዳ​ታይ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


የአባቱን ትምህርት ከመጠበቅ የሚከለከል ልጅ፥ ክፉ ቃልን ይማራል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios