Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ል​ል​ታ​ውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእ​ል​ልታ ድምፅ ምን​ድን ነው?” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረ​ሰች አስ​ተ​ዋሉ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፍልስጥኤማውያንም ይህን ታላቅ ጩኸት ሲሰሙ፣ “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ሁሉ ጩኸት ምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቁ። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ሰፈር መምጣቱን በተረዱ ጊዜ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፍልስጥኤማውያንም ይህን ታላቅ የሆታ ድምፅ ሲሰሙ፥ “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ሁሉ የሆታ ድምፅ ምንድነው?” ሲሉ ጠየቁ። የጌታም ታቦት ወደ ሰፈር መምጣቱን በተረዱ ጊዜ፤

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፍልስጥኤማውያንም ያንን የእልልታ ድምፅ ሰምተው “በዕብራውያን ሰፈር የምንሰማው ይህ ታላቅ የእልልታ ድምፅ ምን ይሆን?” ተባባሉ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዕብራውያን ሰፈር መምጣቱንም ባወቁ ጊዜ፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ፍልስጥኤማውያንም የእልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፦ በዕብራውያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእልልታ ድምፅ ምንድር ነው? አሉ። የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደገባ አስተዋሉ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 4:6
4 Referências Cruzadas  

የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች፥ “እነ​ዚህ በኋላ የሚ​ሄ​ዱት እነ​ማን ናቸው?” አሉ፤ አን​ኩ​ስም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን አለ​ቆች፥ “ይህ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የሳ​ኦል አገ​ል​ጋይ ዳዊት ነው፤ እርሱ በእ​ነ​ዚህ ሁለት ዓመ​ታት ከእኛ ጋር ነበረ፤ ወደ እኔም ከተ​ጠ​ጋ​በት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ሰፈር በገ​ባች ጊዜ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ታላቅ እል​ልታ አደ​ረጉ፤ ምድ​ሪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ፈር​ተው፥ “አማ​ል​ክት ወደ እነ​ርሱ ወደ ሰፈር መጥ​ተ​ዋል” አሉ። ደግ​ሞም እን​ዲህ አሉ፥ “ወዮ​ልን! አቤቱ፥ ዛሬ አድ​ነን፤ ከዚህ አስ​ቀ​ድሞ እን​ዲህ ያለ ነገር አል​ሆ​ነ​ምና።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios