Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 28:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ንጉ​ሡም፥ “አት​ፍሪ ፤ ንገ​ሪኝ፤ ማንን አየሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም፥ “አማ​ል​ክት ከም​ድር ሲወጡ አየሁ” አለ​ችው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ንጉሡም፣ “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትዮዋም፣ “መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ” አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ንጉሡም፥ “አትፍሪ፤ ለመሆኑ ምን እያየሽ ነው?” አላት። ሴትዮዋም፥ “አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ” አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ንጉሡም “አይዞሽ አትፍሪ! ይልቅስ የምታዪው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃት። እርስዋም “እኔ አንድ መለኮታዊ ግርማ ያለው ከመቃብር ሲወጣ እያየሁ ነኝ” አለችው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ንጉሡም፦ አትፍሪ፥ ያየሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፦ አማልክት ከምድር ሲወጡ አየሁ አለችው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 28:13
6 Referências Cruzadas  

“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


እርሱ ስለ አንተ ከሕ​ዝቡ ጋር ይነ​ጋ​ገ​ራል፤ እርሱ አፍ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለህ።


ሴቲ​ቱም ሳሙ​ኤ​ልን ባየች ጊዜ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸች፤ ሴቲ​ቱም ሳኦ​ልን፥ “አንተ ሳኦል ስት​ሆን ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” ብላ ተና​ገ​ረ​ችው።


እር​ሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማ​ግሌ ሰው ከም​ድር ወጣ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ተጐ​ና​ጽ​ፎ​አል” አለች። ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊ​ቱም ወደ ምድር ጐን​በስ ብሎ ሰገ​ደ​ለት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios