Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 28:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለሰ​ልፍ ሰበ​ሰቡ፤ አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን፥ “አን​ተና ሰዎ​ችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እን​ድ​ት​ወጡ በር​ግጥ ዕወቅ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያ ዘመን ፍልስጥኤማውያን፣ እስራኤልን ለመውጋት ሰራዊታቸውን ሰበሰቡ። አንኩስም ዳዊትን፣ “አንተና ሰዎችህ ዐብራችሁኝ ለጦርነት መውጣት እንዳለባችሁ ዕወቁ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያን ዘመን ፍልስጥኤማውያን፥ እስራኤልን ለመውጋት ሠራዊታቸውን ሰበሰቡ። አኪሽም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ አብራችሁኝ ለጦርነት መውጣት እንዳለባችሁ ትረዳኛለህ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት የጦር ሠራዊታቸውን ሰበሰቡ፤ አኪሽም ዳዊትን “አንተና ተከታዮችህ ከእኔ ጐን ተሰልፋችሁ መዋጋት እንደሚገባችሁ በእርግጥ ዕወቅ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፥ በዚያ ወራት ከእስራኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ጭፍሮቻቸውን ለሰልፍ ሰበሰቡ፥ አንኩስም ዳዊትን፦ አንተና ሰዎችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እንድትወጡ በእርግጥ እወቅ አለው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 28:1
7 Referências Cruzadas  

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ጭፍ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ለጦ​ር​ነት ሰበ​ሰቡ፤ ራሳ​ቸ​ውም በይ​ሁዳ በሰ​ኮት ተሰ​በ​ሰቡ፤ በሰ​ኮ​ትና በዓ​ዜቃ መካ​ከል በኤ​ፌ​ር​ሜም ሰፈሩ።


አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፤ ተዋ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ መሴፋ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ በሰሙ ጊዜ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዘመቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሰም​ተው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ፈሩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios