Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 24:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትም በዚህ ቃል ሰዎ​ቹን ከለ​ከ​ላ​ቸው። በሳ​ኦ​ልም ላይ ተነ​ሥ​ተው ይገድ​ሉት ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸ​ውም፤ ሳኦ​ልም ከዋ​ሻው ተነ​ሥቶ መን​ገ​ዱን ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም ዳዊት ከዋሻው ወጥቶ ሳኦልን፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጠራው። ሳኦልም ወደ ኋላው ዞር ባለ ጊዜ፣ ዳዊት ወደ መሬት ጐንበስ ብሎ እጅ ሲነሣው ተመለከተ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከእርሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፥ ከዋሻውም ወጣ፥ ከሳኦልም በኋላ፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ብሎ ጮኸ፥ ሳኦልም ወደ ኋላው ተመለከተ፥ ዳዊትም ወደ ምድር ተጎንብሶ እጅ ነሣ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 24:8
11 Referências Cruzadas  

አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦


ቤር​ሳ​ቤ​ህም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ላይ ተደ​ፍታ ለን​ጉሡ ሰገ​ደ​ችና፥ “ጌታዬ ንጉሥ ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ይኑር” አለች።


“አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።


ለሁ​ሉም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው አድ​ርጉ፤ ግብር ለሚ​ገ​ባው ግብ​ርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚ​ገ​ባው ቀረ​ጥን ስጡ፤ ዐሥ​ራት ለሚ​ገ​ባው ዐሥ​ራ​ትን ስጡ፤ ሊፈ​ሩት የሚ​ገ​ባ​ውን ፍሩ፤ ክብር የሚ​ገ​ባ​ው​ንም አክ​ብሩ።


ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ብላ​ቴ​ና​ውም በሄደ ጊዜ ዳዊት ከኤ​ር​ገብ ተነሣ፤ በም​ድ​ርም ላይ በግ​ን​ባሩ ተደፋ፤ ሦስት ጊዜም ሰገደ፤ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ፤ ለረ​ዥም ሰዓ​ትም ተላ​ቀሱ።


ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባው ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀ​ባው በጌ​ታዬ ላይ እን​ዲህ ያለ​ውን ነገር አደ​ርግ ዘንድ፥ እጄ​ንም እጥ​ል​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኔ ያር​ቀው” አላ​ቸው።


ከእ​ር​ሱም በኋላ ዳዊት ደግሞ ተነሣ፤ ከዋ​ሻ​ውም ወጣ፤ ከሳ​ኦ​ልም በኋላ፦“ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” ብሎ ጮኸ፤ ሳኦ​ልም ወደ ኋላው ተመ​ለ​ከተ፤ ዳዊ​ትም ወደ ምድር ተጐ​ን​ብሶ እጅ ነሣ።


ሳኦ​ልም የዳ​ዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድም​ፅህ ነውን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪ​ያህ ነኝ” አለው።


እር​ሱም፥ “ምን አየሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ቀጥ ያለ ሽማ​ግሌ ሰው ከም​ድር ወጣ፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ተጐ​ና​ጽ​ፎ​አል” አለች። ሳኦ​ልም ሳሙ​ኤል እንደ ሆነ ዐወቀ፤ በፊ​ቱም ወደ ምድር ጐን​በስ ብሎ ሰገ​ደ​ለት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios