Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 23:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትና ስድ​ስት መቶ የሚ​ሆኑ ሰዎ​ችም ተነ​ሥ​ተው ከቂ​አላ ወጡ፤ ወደ​ሚ​ሄ​ድ​በ​ትም ይከ​ተ​ሉት ነበር። ሳኦ​ልም ዳዊት ከቂ​አላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለ​ዚ​ህም ከመ​ው​ጣት ቀረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፣ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፥ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ በሙሉ ወዲያውኑ ቀዒላን ለቀው ለመሄድ ተንቀሳቀሱ፤ ሳኦልም ዳዊት ከቀዒላ አምልጦ መሄዱን በሰማ ጊዜ የነበረውን ዕቅድ ተወ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎችም ተነሥተው ከቅዒላ ወጡ፥ መሄድም ወደሚችሉበት ሄዱ። ሳኦልም ዳዊት ከቅዒላ እንደ ሸሸ ሰማ፥ ስለዚህም ከመውጣት ቀረ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 23:13
7 Referências Cruzadas  

ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ሁሉ ተከ​ተ​ሉት፤ ኬል​ቲ​ያ​ው​ያ​ንና ፌል​ታ​ው​ያ​ንም ሁሉ በም​ድረ በዳ በወ​ይራ ሥር ቆሙ። ሕዝ​ቡም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእ​ርሱ ጋር ያሉ ሰዎ​ችም ሁሉ ስድ​ስት መቶ ነበሩ። ከእ​ርሱ ጋር ፌል​ታ​ው​ያ​ንና ኬል​ቲ​ያ​ው​ያን፥ በእ​ግ​ራ​ቸው ከጌት የመጡ ስድ​ስት መቶ ጌታ​ው​ያ​ንም ነበሩ። በን​ጉ​ሡም ፊት ይሄዱ ነበር።


የመ​ጣ​ኸው ትና​ንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙ​ር​ህን? እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንተ ግን ተመ​ለስ፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ህ​ንም ከአ​ንተ ጋር መል​ሳ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱ​ንና እው​ነ​ቱን ያድ​ር​ግ​ልህ” አለው።


የተ​ን​ኰ​ለ​ኞ​ችን ምክር ይለ​ው​ጣል፥ እጆ​ቻ​ቸ​ውም ቅን አይ​ሠ​ሩም።


በነ​ፋስ ፊት እን​ዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው።


የተ​ጨ​ነ​ቀም ሁሉ፥ ዕዳም ያለ​በት ሁሉ፥ የተ​ከ​ፋም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​ባ​ሰበ፤ እር​ሱም በላ​ያ​ቸው አለቃ ሆነ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ።


ዳዊ​ትም ሰዎ​ቹን፥ “ሁላ​ችሁ ሰይ​ፋ​ች​ሁን ታጠቁ” አላ​ቸው። ሁሉም ሰይ​ፋ​ቸ​ውን ታጠቁ፤ ዳዊ​ትም ሰይ​ፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎ​ችም ዳዊ​ትን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ሁለት መቶ​ውም በጓ​ዛ​ቸው ዘንድ ተቀ​መጡ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios