Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 20:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሳኦ​ልም ሊገ​ድ​ለው በዮ​ና​ታን ላይ ጦሩን አነሣ፤ ዮና​ታ​ንም አባቱ ዳዊ​ትን ይገ​ድ​ለው ዘንድ ያች ክፉ ነገር እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዐወቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፣ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቈርጦ መነሣቱን ዐወቀ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሳኦልም ዮናታንን ለመግደል ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ ዮናታን፥ አባቱ ዳዊትን ለመግደል ቆርጦ መነሣቱን ዐወቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ከዚህም የተነሣ ዮናታንን ለመግደል የያዘውን ጦር ወረወረበት፤ ስለዚህም ዮናታን አባቱ ሳኦል ዳዊትን ለመግደል ቊርጥ ውሳኔ ማድረጉን አረጋገጠ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሳኦልም ሊወጋው ጦሩን ወረወረበት፥ ዮናታንም አባቱ ዳዊትን ፈጽሞ ሊገድለው እንደ ፈቀደ አወቀ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 20:33
5 Referências Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ሊገ​ድ​ለው ወደደ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ተነ​ሥቶ ወደ ግብፅ ሀገር፥ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሱስ​ቀም ኰብ​ልሎ ሄደ፥ ሰሎ​ሞ​ንም እስ​ኪ​ሞት ድረስ በግ​ብፅ ተቀ​መጠ።


ሳኦ​ልም፥ “ዳዊ​ትን ከግ​ንቡ ጋር አጣ​ብቄ እመ​ታ​ዋ​ለሁ” ብሎ ጦሩን ወረ​ወረ። ዳዊ​ትም ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።


ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ከግ​ንብ ጋር ያጣ​ብ​ቀው ዘንድ ጦሩን ወረ​ወረ፤ ዳዊ​ትም ከሳ​ኦል ፊት ዘወር አለ፤ ጦሩም በግ​ንቡ ውስጥ ተተ​ከለ፤ በዚ​ያም ሌሊት ዳዊት ሸሸቶ አመ​ለጠ።


አባቱ በእ​ርሱ ላይ ክፉ ነገ​ርን ሊያ​ደ​ርግ ስለ ቈረጠ ዮና​ታን ስለ ዳዊት አዝ​ኖ​አ​ልና እጅግ ተቈ​ጥቶ ከማ​ዕዱ ተነሣ፤ በመ​ባ​ቻ​ውም በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን ግብር አል​በ​ላም።


እር​ሱም፦ መል​ካም ነው ቢል ለእኔ ለባ​ሪ​ያህ ሰላም ይሆ​ናል፤ ቢቈጣ ግን ክፋት ከእ​ርሱ ዘንድ በእኔ ላይ እንደ ተቈ​ረ​ጠች ዕወቅ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios