Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 20:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከመ​ባ​ቻም በኋላ በማ​ግ​ሥቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን የዳ​ዊት ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ፤ ሳኦ​ልም ልጁን ዮና​ታ​ንን፥ “የእ​ሴይ ልጅ ትና​ትና ዛሬ ወደ ግብር ያል​መጣ ስለ​ምን ነው?” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 በማግስቱም፣ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፣ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፣ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በማግስቱም፥ ወር በገባ በሁለተኛው ቀን የዳዊት መቀመጫ ባዶ ነበር፤ ከዚያም ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ “የእሴይ ልጅ ትናንትናም፥ ዛሬም ግብር ላይ ያልተገኘው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አዲስ ጨረቃ የታየችበት በዓል ካለፈ በኋላም በተከታዩ ቀን የዳዊት ወንበር ባዶ ነበር፤ ስለዚህ ሳኦል ልጁን ዮናታንን “የእሴይ ልጅ ትናንትም፥ ዛሬም ወደዚህ ግብዣ ያልመጣው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ከመባቻም በኋላ በማግሥቱ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶውን ነበረ፥ ሳኦልም ልጁን ዮናታንን፦ የእሴይ ልጅ ትናንትና ወይም ዛሬ ግብር ሊበላ ያልመጣ ስለ ምን ነው? አለው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 20:27
12 Referências Cruzadas  

ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ፥ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን?


በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥


ሳኦ​ልም፥ “ዳዊ​ትን ከግ​ንቡ ጋር አጣ​ብቄ እመ​ታ​ዋ​ለሁ” ብሎ ጦሩን ወረ​ወረ። ዳዊ​ትም ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።


ሳኦ​ልም፥ “እገ​ድ​ለው ዘንድ ዳዊ​ትን ከነ​አ​ል​ጋው” አም​ጡ​ልኝ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ቹን ወደ ዳዊት ላከ።


ሳኦ​ልም፥ “አንድ ነገር ሆኖ ይሆ​ናል፤ ምን​አ​ል​ባ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም ይሆ​ናል፤ በእ​ው​ነ​ትም ንጹሕ አይ​ደ​ለም” ብሎ አስ​ቦ​አ​ልና በዚያ ቀን ምንም አል​ተ​ና​ገ​ረም።


ዮና​ታ​ንም ለሳ​ኦል፥ “ዳዊት ወደ ከተ​ማው ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ ነግ​ሮኝ ተሰ​ና​ብ​ቶ​ኛል።


ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በን​ጉ​ሥም አጠ​ገብ ለምሳ አል​ቀ​መ​ጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እን​ድ​ሸ​ሸግ አሰ​ና​ብ​ተኝ ።


ናባ​ልም ተነ​ሥቶ ለዳ​ዊት ብላ​ቴ​ኖች መለ​ሰ​ላ​ቸው እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእ​ሴ​ይስ ልጅ ማን ነው? እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ከጌ​ቶ​ቻ​ቸው የኰ​በ​ለሉ አገ​ል​ጋ​ዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios