Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 17:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን በወ​ን​ጭ​ፍና በድ​ን​ጋይ አሸ​ነ​ፈው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም መትቶ ገደለ ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ ሰይፍ አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 በዚህ ሁኔታ ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ብቻ ፍልስጥኤማዊውን አሸነፈው፤ በእጁም ሰይፍ ሳይዝ ፍልስጥኤማዊውን መታው፤ ገደለውም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 በዚህም ዐይነት ዳዊት በወንጭፍና በድንጋይ ጎልያድን መትቶ በመግደል ድል አደረገ! በእጁም ሰይፍ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው፥ ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለ፥ በዳዊትም እጅ ሰይፍ አልነበረም።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 17:50
9 Referências Cruzadas  

የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።


ከእ​ር​ሱም በኋላ የሐ​ናት ልጅ ሴሜ​ጋር ተነሣ፤ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ስድ​ስት መቶ ሰው በበሬ መው​ጊያ ገደለ፤ እር​ሱም ደግሞ እስ​ራ​ኤ​ልን አዳነ።


ስለ​ዚ​ህም በማ​ኪ​ማስ ጦር​ነት ጊዜ ሰይ​ፍና ጦር ከሳ​ኦ​ልና ከዮ​ና​ታን ጋር በነ​በሩ ሕዝብ ሁሉ እጅ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ብቻ በሳ​ኦ​ልና በልጁ በዮ​ና​ታን ዘንድ ተገኘ።


ዳዊ​ት​ንም ሰይ​ፉን በል​ብሱ ላይ አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ ዳዊ​ትም አን​ድና ሁለት ጊዜ ሲራ​መድ ደከመ። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “አለ​መ​ድ​ሁ​ምና በዚህ መሄድ አል​ች​ልም” አለው። ከላ​ዩም አወ​ለ​ቁ​ለት።


ዳዊ​ትም እጁን ወደ ኮሮ​ጆው አግ​ብቶ አንድ ድን​ጋይ ወሰደ፤ ወነ​ጨ​ፈ​ውም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ግን​ባ​ሩን መታው፤ ድን​ጋ​ዩም ጥሩ​ሩን ዘልቆ በግ​ን​ባሩ ተቀ​ረ​ቀረ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ በፊቱ ተደፋ።


ዳዊ​ትም ሮጦ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ላይ ቆመ፤ ሰይ​ፉ​ንም ይዞ ከሰ​ገ​ባው መዘ​ዘው፤ ገደ​ለ​ውም፤ ራሱ​ንም ቈረ​ጠው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ዋና​ቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ሸሹ።


ነፍ​ሱ​ንም በእጁ ጥሎ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ገደለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ታላቅ መድ​ኀ​ኒት አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ አይ​ተው ደስ አላ​ቸው፤ በከ​ንቱ ዳዊ​ትን ትገ​ድ​ለው ዘንድ ስለ​ምን በን​ጹሕ ደም ላይ ትበ​ድ​ላ​ለህ?”


ካህ​ኑም፥ “በኤላ ሸለቆ የገ​ደ​ል​ኸው የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው የጎ​ል​ያድ ሰይፍ እነሆ፥ በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊያ ተጠ​ቅ​ልላ አለች፤ የም​ት​ወ​ስ​ዳት ከሆነ ውሰ​ዳት፤ ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከዚህ የለ​ምና” አለው። ዳዊ​ትም፥ “ከእ​ር​ስዋ በቀር ሌላ ከሌለ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው። እር​ሱም ሰጠው።


ሳኦ​ልም አለ፥ “እና​ንተ ስለ እኔ አዝ​ና​ች​ኋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ረ​ካ​ችሁ ሁኑ፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios