Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 17:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ዳዊ​ትም ዕቃ​ውን በዕቃ ጠባ​ቂው እጅ አኖ​ረው፤ ወደ​ሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ሮጦ ሄደ፤ የወ​ን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ደኅ​ን​ነት ጠየቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዳዊት ዕቃውን ከስንቅ ጠባቂው ዘንድ አስቀምጦ ወደ ጦሩ ግንባር ሮጠ፤ ወንድሞቹንም አግኝቶ ደኅንነታቸውን ጠየቀ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዳዊትም የያዘውን ምግብ ለስንቅ ጠባቂው ትቶ ወደ ጦሩ ግንባር እየሮጠ ወደ ወንድሞቹ ሄደ፤ ስለ ደኅንነታቸውም ጠየቃቸው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዳዊትም ዕቃውን በዕቃ ጠባቂው እጅ አኖረው፥ ወደ ሠራዊቱም ሮጠ፥ የወንድሞቹንም ደኅንነት ጠየቀ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 17:22
11 Referências Cruzadas  

እር​ሱም፥ “ሄደህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬ​አ​ቸ​ው​ንም አም​ጣ​ልኝ” አለው። ወደ ኬብ​ሮ​ንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬ​ምም መጣ።


ኦር​ዮም ደርሶ ወደ እርሱ በገባ ጊዜ ዳዊት የኢ​ዮ​አ​ብ​ንና የሕ​ዝ​ቡን ደኅ​ን​ነት፥ ሰል​ፉም እን​ዴት እንደ ሆነ ጠየ​ቀው።


ሙሴም አማ​ቱን ሊገ​ናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመ​ውም፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ሰላ​ምታ ተሰ​ጣጡ፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ገቡ።


ወደ አን​ጋይ ከተማ ይመ​ጣል፤ በመ​ጌ​ዶን በኩል ያል​ፋል፤ በማ​ክ​ማ​ስም ውስጥ ዕቃ​ውን ያኖ​ራል፤


ከመ​ን​ገ​ዱም ፈቀቅ ብለው ወደ ጐል​ማ​ሳው ሌዋዊ ቤት ወደ ሚካ ቤት መጡ፤ ሰላ​ም​ታም ሰጡት።


እነ​ር​ሱም ተመ​ል​ሰው ሄዱ፤ ቤተ ሰቡን፥ ገን​ዘ​ቡ​ንና ሀብ​ቱ​ንም ሁሉ፥ በፊ​ታ​ቸው አድ​ር​ገው ወሰዱ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሠራ​ዊ​ትም ፊት ለፊት ተሰ​ላ​ል​ፈው ነበር።


ዳዊ​ትም ዐሥር ብላ​ቴ​ኖ​ችን ላከ፤ ለብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም አለ፥ “ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ወጥ​ታ​ችሁ ወደ ናባል ሂዱ፤ በስ​ሜም ሰላም በሉት፤


ዳዊ​ትም ደክ​መው ዳዊ​ትን ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ወዳ​ል​ቻሉ፥ በቦ​ሦር ወንዝ ወዳ​ስ​ቀ​ራ​ቸው ወደ ሁለቱ መቶ ሰዎች መጣ፤ እነ​ር​ሱም ዳዊ​ትን ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ ሊቀ​በሉ ወጡ፤ ዳዊ​ትም ወደ ሕዝቡ በቀ​ረበ ጊዜ ደኅ​ን​ነ​ቱን ጠየ​ቁት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios