Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 1:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እር​ስ​ዋም ከእ​ርሱ ጋር አንድ የሦ​ስት ዓመት ወይ​ፈን፥ እን​ጀራ፥ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁ​ማዳ የወ​ይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወጣች። በሴ​ሎም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገባች። ልጃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ልጁ ጡት በተወ ጊዜ ከርሱ ጋራ አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄትና አንድ አቍማዳ የወይን ጠጅ ወስዳ፣ በሴሎ ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣችው፣ ልጁም ገና ሕፃን ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ልጁ ጡት በተወ ጊዜ ከእርሱ ጋር አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄትና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ወስዳ፥ በሴሎ ወዳለው ወደ ጌታ ቤት አመጣችው፤ ልጁም ገና ሕፃን ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ጡት ካስጣለችውም በኋላ ወደ ሴሎ ይዛው ወጣች፤ ከእርሱም ጋር የሦስት ዓመት ኰርማ ዐሥር ኪሎ ዱቄትና አንድ አቁማዳ ሙሉ የወይን ጠጅ ይዛ ሄደች፤ ሳሙኤልንም ገና በልጅነቱ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ጡትም በተወ ጊዜ ከእርስዋ ጋር እርሱንና አንድ የሦስት ዓመት ወይፈን፥ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ዱቄት፥ አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ይዛ ወደ ሴሎ ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣችው፥ ሕፃኑም ገና ታናሽ ነበረ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 1:24
9 Referências Cruzadas  

ሕፃ​ኑም አደገ፤ ጡት​ንም አስ​ጣ​ሉት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ጡት ባስ​ጣ​ለ​በት ቀን ትልቅ ግብ​ዣን አደ​ረገ።


የቴ​ቄ​ም​ናስ እኅት ወንድ ልጅ ጌን​ባ​ትን ለአ​ዴር ወለ​ደ​ች​ለት፤ ቴቄ​ም​ና​ስም በፈ​ር​ዖን ልጆች መካ​ከል አሳ​ደ​ገ​ችው፤ ጌን​ባ​ትም በፈ​ር​ዖን ልጆች መካ​ከል ነበረ።


ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህም አለ “መንግሥተ ሰማያት ሁሉ እስኪቦካ ድረስ ሴት ወስዳ በሦስት መስፈሪያ ዱቄት የሸሸገችውን እርሾ ትመስላለች።”


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


በዓ​መት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰ​ባቱ ሱባ​ዔም በዓል፥ በዳ​ስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ይታይ፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በሴሎ ተሰ​በ​ሰቡ፤ በዚ​ያም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ተከሉ፤ ምድ​ሩም ጸጥ ብሎ ተገ​ዛ​ላ​ቸው።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios