Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ሳሙኤል 1:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሐናም በል​ብዋ ትና​ገር ነበር፤ ድም​ፅ​ዋም ሳይ​ሰማ ከን​ፈ​ር​ዋን ታን​ቀ​ሳ​ቅስ ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከ​ረች ቈጠ​ራት።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሷም በልቧ ትጸልይ ስለ ነበር፤ ከንፈሯ ይንቀሳቀስ እንጂ ድምፅዋ አይሰማም ነበር፤ ዔሊም እንደ ሰከረች አድርጎ ቈጠራት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሐናም በልቧ ትጸልይ የነበረ በመሆኑ፥ ከንፈሯ ይንቀሳቀስ እንጂ ድምጿ አይሰማም ነበር፤ ስለዚህ ዔሊ እንደ ሰከረች አድርጎ ቆጠራት

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሐና ምንም ድምፅ ሳታሰማ ከንፈርዋን እያንቀሳቀሰች በልብዋ በመናገር ትጸልይ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ዔሊ በመጠጥ የሰከረች መሰለው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፥ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፥ ዔሊም እንደ ሰከረች ቈጠራት።

Ver Capítulo Cópia de




1 ሳሙኤል 1:13
8 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡም፥ “ምን ትለ​ም​ነ​ኛ​ለህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አም​ላክ ጸለ​ይሁ።


አቤቱ፥ እኔ በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለ​ሁና ፍረ​ድ​ልኝ፤ እን​ዳ​ል​ደ​ክም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመ​ንሁ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፣ እነርሱም ይበሉአቸዋል፥ የወንጭፉንም ድንጋዮች ይረግጣሉ፣ እንደ ወይን ጠጅም ይጠጡአቸዋል፥ እንደ ጥዋዎችም እንደ መሠዊያም ማዕዘኖች የተሞሉ ይሆናሉ።


እኩ​ሌ​ቶቹ ግን “እነ​ዚ​ህስ ጉሽ ጠጅ ጠግ​በው ሰክ​ረ​ዋል” ብለው ሳቁ​ባ​ቸው።


መን​ፈስ ቅዱ​ስም ከድ​ካ​ማ​ችን ይረ​ዳ​ናል፤ እን​ግ​ዲ​ያስ ተስ​ፋ​ች​ንን ካላ​ወ​ቅን ጸሎ​ታ​ችን ምን​ድ​ነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ መከ​ራ​ች​ንና ስለ ችግ​ራ​ችን ይፈ​ር​ድ​ል​ናል።


በሁሉ ያቻ​ች​ላል፤ በሁ​ሉም ያስ​ተ​ማ​ም​ናል፤ በሁ​ሉም ተስፋ ያስ​ደ​ር​ጋል፥ በሁ​ሉም ያስ​ታ​ግ​ሣል።


ጸሎ​ቷ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ባበ​ዛች ጊዜ፥ ካህኑ ዔሊ አፍ​ዋን ይመ​ለ​ከት ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios