Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም በዝ​ግ​ባና በጥድ እን​ጨት፥ በወ​ር​ቅና በሚ​ሻ​ውም ሁሉ ሰሎ​ሞ​ንን ረድ​ቶት ነበር። ያን​ጊ​ዜም ንጉሡ ሰሎ​ሞን በገ​ሊላ ምድር ያሉ​ትን ሃያ ከተ​ሞች ለኪ​ራም ሰጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ንጉሥ ሰሎሞን በገሊላ የሚገኙትን ሃያ ከተሞች ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም ሰጠው፤ ንጉሡ ይህን ያደረገውም፣ የሚያስፈልገውን ሁሉ ዝግባ፣ ጥድና ወርቅ ኪራም ሰጥቶት ስለ ነበር ነው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞችን ለኪራም ሰጠው።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዚህ ሁሉ ሥራ ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስ ዛፍና ዝግባ ከብዙ ወርቅ ጋር ሰጥቶት ነበር፤ ሥራውም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ሰሎሞን በገሊላ ምድር የሚገኙትን ኻያ ታናናሽ ከተሞች ለኪራም ሰጠው፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ንጉሡ ሰሎሞን በገሊላ ምድር ያሉትን ሃያ ከተሞች ለኪራም ሰጠው። የጢሮስም ንጉሥ ኪራም የሚሻውን ያህል የዝግባና የጥድ እንጨት የሚሻውንም ያህል ወርቅ ሁሉ ለሰሎሞን ሰጥቶት ነበር።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 9:11
9 Referências Cruzadas  

ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት ሁለ​ቱን ቤቶች በሠ​ራ​በት በሃያ ዓመት ውስጥ፥


ኪራ​ምም ሰሎ​ሞን የሰ​ጠ​ውን ከተ​ሞች ያይ ዘንድ ከጢ​ሮስ ወጣ፤ ወደ ገሊ​ላም ሄደ፤ ደስም አላ​ሰ​ኙ​ትም።


ኪራ​ምም መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ለሰ​ሎ​ሞን አመጣ።


እኛም ከሊ​ባ​ኖስ የም​ት​ሻ​ውን ያህል እን​ጨት እን​ቈ​ር​ጣ​ለን፤ በታ​ን​ኳም አድ​ር​ገን በባ​ሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እን​ል​ካ​ለን፤ አን​ተም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ታስ​ወ​ስ​ደ​ዋ​ለህ።”


ኪራም ለሰ​ሎ​ሞን የሰ​ጠ​ውን ከተ​ሞች ሰሎ​ሞን ሠራ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች አኖ​ረ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የሰ​ሎ​ሞን ምር​ኮ​ኞ​ችን በኤ​ዶ​ም​ያስ ዘግ​ተ​ዋ​ልና፥ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ንም ቃል ኪዳን አላ​ሰ​ቡ​ምና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጢ​ሮስ ኀጢ​አት አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


በን​ፍ​ታ​ሌም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር በገ​ሊላ ቃዴ​ስን፥ በኤ​ፍ​ሬ​ምም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ሴኬ​ምን፥ በይ​ሁ​ዳም ባለው በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ኬብ​ሮን የም​ት​ባ​ለ​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ለዩ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios