Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 8:56 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

56 “እንደ ተና​ገ​ረው ተስፋ ሁሉ ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ዕረ​ፍ​ትን የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፥ በባ​ሪ​ያው በሙሴ ቃል ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ቃል ሁሉ ያጐ​ደ​ለው አን​ድም ቃል የለም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

56 “በሰጠው ተስፋ መሠረት ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን ለሰጠ እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው፤ በባሪያው በሙሴ አማካይነት ከተሰጠው መልካም ተስፋ ሁሉ አንድም ቃል አልቀረምና።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

56 “በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

56 “በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

56 “እንደ ተናገረው ተስፋ ሁሉ ለሕዝቡ ለእስራኤል ዕረፍትን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን! በባሪያው በሙሴ ከሰጠው ከመልካም ተስፋ ሁሉ አንድ ቃል አልወደቀም።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 8:56
15 Referências Cruzadas  

እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ክ​አብ ቤት ላይ ከተ​ና​ገ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በም​ድር ላይ አን​ዳች እን​ዳ​ይ​ወ​ድቅ አሁን ዕወቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ሪ​ያው በኤ​ል​ያስ ቃል የተ​ና​ገ​ረ​ውን አድ​ር​ጎ​አል” አላ​ቸው።


ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ረክ። ሕዝቡ ሁሉ አሜን ይበሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ስ​ግኑ።


እነሆ፥ ልጅ ይወ​ለ​ድ​ል​ሃል፤ የዕ​ረ​ፍት ሰውም ይሆ​ናል፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ አሳ​ር​ፈ​ዋ​ለሁ፤ ስሙ ሰሎ​ሞን ይባ​ላ​ልና፥ በዘ​መ​ኑም ሰላ​ም​ንና ጸጥ​ታን ለእ​ስ​ራ​ኤል እሰ​ጣ​ለሁ።


በይ​ሁ​ዳም ምሽ​ጎች ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕረ​ፍት ስለ ሰጠው ምድ​ሪቱ ጸጥ ብላ ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።


ዮቶ​ርም፥ “ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ ሕዝ​ቡን የአ​ዳነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነው።


ሰማ​ይና ምድር ያል​ፋል፤ ቃሌ ግን አያ​ል​ፍም።


ዮር​ዳ​ኖ​ስን ግን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ያ​ወ​ር​ሳ​ችሁ ምድር በተ​ቀ​መ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥ ያለ ፍር​ሀ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ ከከ​በ​ቡ​አ​ችሁ ጠላ​ቶች ሁሉ ዕረ​ፍት በሰ​ጣ​ችሁ ጊዜ፥


እና​ን​ተም፥ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ች​ሁም፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ክፍ​ልና ርስት ስለ​ሌ​ለው በደ​ጆ​ቻ​ችሁ ውስጥ የተ​ቀ​መ​ጠው ሌዋ​ዊም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ይኸ​ውም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ እና​ንተ፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን እስ​ኪ​ያ​ሳ​ርፍ ድረስ፥ እነ​ር​ሱም ደግሞ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ምድር እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ነው። ከዚ​ያም በኋላ ሁላ​ችሁ ወደ ሰጠ​ኋ​ችሁ ርስት ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ።


ሳሙ​ኤ​ልም አደገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ ከቃ​ሉም አን​ዳች በም​ድር ላይ አይ​ወ​ድ​ቅም ነበር።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios