Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 8:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ሃት ምድር ላይ በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይፈ​ሩህ ዘንድ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ይኸውም እነርሱ ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ፣ አንተን እንዲፈሩህ ነው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 በዚህም ዓይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በዚህም ዐይነት ሕዝብህ ለቀድሞ አባቶቻችን ርስት አድርገህ በሰጠሃቸው ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለአንተ ታዛዦች እንዲሆኑና እንዲያከብሩህ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 8:40
18 Referências Cruzadas  

እር​ሱም፥ “በብ​ላ​ቴ​ናው ላይ እጅ​ህን አት​ዘ​ርጋ፤ አን​ዳ​ችም አታ​ድ​ር​ግ​በት፤ ለም​ት​ው​ድ​ደው ልጅህ ከእኔ አል​ራ​ራ​ህ​ለ​ት​ምና አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ፈራ እን​ደ​ሆ​ንህ አሁን ዐው​ቄ​አ​ለሁ” አለው።


በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ይቅ​ርም በል፤ አንተ ብቻ የሰ​ውን ልጆች ሁሉ ልብ ታው​ቃ​ለ​ህና ልቡን ለም​ታ​ው​ቀው ሰው ሁሉ እንደ መን​ገዱ ሁሉ መጠን ክፈ​ለ​ውና ስጠው።


“ከሕ​ዝ​ብ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ስምህ ከሩቅ ሀገር ቢመጣ፥


ሙሴም ለሕ​ዝቡ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊፈ​ት​ና​ችሁ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም እን​ዳ​ት​ሠሩ እር​ሱን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ያድር ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና አት​ፍሩ” አላ​ቸው።


ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ል​ሰው አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ዳዊ​ትን ይፈ​ል​ጋሉ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ቸር​ነ​ቱን ያስ​ቡ​ታል።


እር​ሱም ጻድ​ቅና ከነ​ቤተ ሰቡ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ነበር፤ ለሕ​ዝ​ቡም ብዙ ምጽ​ዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወ​ት​ርም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር።


በይ​ሁዳ፥ በሰ​ማ​ር​ያና በገ​ሊላ ያሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ሁሉ በሰ​ላም ኖሩ፤ ታነ​ጹም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በመ​ፍ​ራት ጸን​ተው ኖሩ፤ ሕዝ​ቡም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ አጽ​ና​ኝ​ነት በዙ።


“በም​ድር ላይ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሷት ዘንድ በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ሀገር ታደ​ር​ጉት ዘንድ የም​ት​ጠ​ብ​ቁት ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።


አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል በስ​ሙም ማል።


እና​ንተ፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ች​ሁም በዕ​ድ​ሜ​አ​ችሁ ሁሉ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈር​ታ​ችሁ እኔ ለእ​ና​ንተ ያዘ​ዝ​ሁ​ትን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ ዕድ​ሜ​አ​ች​ሁም ይረ​ዝም ዘንድ፤


ስለ​ዚህ የማ​ይ​ና​ወጥ መን​ግ​ሥ​ትን ስለ​ም​ን​ቀ​በል በማ​ክ​በ​ርና በፍ​ር​ሀት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ እያ​ሰ​ኘን የም​ና​መ​ል​ክ​በ​ትን ጸጋ እን​ያዝ።


ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ጠን​ካራ እንደ ሆነች የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ያ​ውቁ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ራው ሁሉ እን​ድ​ት​ፈሩ ነው።”


ድምፅም “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤” ሲል ከዙፋኑ ወጣ።


ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩ፤ ያደ​ረ​ገ​ላ​ች​ሁ​ንም ታላቅ ነገር አይ​ታ​ች​ኋ​ልና በፍ​ጹም ልባ​ችሁ በእ​ው​ነት አም​ል​ኩት፤


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios