Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 8:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መል​ካም መን​ገድ በማ​ሳ​የት የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና የሕ​ዝ​ብ​ህን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም ርስት አድ​ር​ገህ ለሰ​ጠ​ሃት ምድር ዝና​ብን ስጥ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የባሪያዎችህን የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ የሚሄዱበትን ቀናውን መንገድ አስተምራቸው፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸውም ምድርህ ላይ ዝናብን አዝንብ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 አንተ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን ስማ፤ የአገልጋዮችህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ቅን የሆነውንም ነገር ማድረግ ይችሉ ዘንድ አስተምራቸው፤ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ሆይ፥ ለዘለዓለም ርስት አድርገህ ለሕዝብህ በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ዝናብ እንዲዘንብ አድርግ።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 አንተ በሰማይ ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለሕዝብህም ርስት አድርገህ ለሰጠሃት ምድር ዝናብ ስጥ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 8:36
28 Referências Cruzadas  

ከብዙ ቀንም በኋላ በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት፥ “ሂድ ለአ​ክ​ዓብ ተገ​ለጥ፤ በም​ድር ላይም ዝናም እሰ​ጣ​ለሁ” የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ኤል​ያስ መጣ።


ኤል​ያ​ስም አክ​ዓ​ብን፥ “የዝ​ናቡ ውሽ​ን​ፍር እጅግ ነውና ተነ​ሥ​ተህ ውጣ፤ ብላም፤ ጠጣም” አለው።


ወዲያ ወዲ​ህም እስ​ኪ​መ​ላ​ለስ ድረስ ሰማዩ በደ​መ​ናና በነ​ፋስ ጨለመ፤ ትል​ቅም ዝናብ ዘነበ፤ አክ​ዓ​ብም በሰ​ረ​ገላ ተቀ​ምጦ እያ​ለ​ቀሰ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ።


አፋ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ አስ​ጥ​ለኝ።


እግ​ሮቼ በቅ​ን​ነት ቆመ​ዋ​ልና፤ አቤቱ፥ በማ​ኅ​በር አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


አቤቱ፥ የቤ​ት​ህን ጌጥ የክ​ብ​ር​ህ​ንም ማደ​ሪያ ቦታ ወደ​ድሁ።


ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ራ​ዋ​ለች፥ በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


አቤቱ፥ በጽ​ድ​ቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላ​ቶቼ መን​ገ​ዴን በፊ​ትህ አቅና።


ሰው​ነ​ቴን በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፥ ስድ​ብ​ንም ሆነ​ብኝ።


የቤ​ትህ ቅን​ዓት በል​ቶ​ኛ​ልና፥ የሚ​ሰ​ድ​ቡ​ህም ስድብ በላዬ ወድ​ቆ​አ​ልና።


ወደ ቀኝም ቢሆን ወደ ግራም ቢሆን በኋ​ላህ በዚህ መን​ገድ እን​ሂድ የሚ​ሉና የሚ​ሳ​ሳቱ ሰዎ​ችን ድምፅ ጆሮ​ዎ​ችህ ይሰ​ማሉ።


በዚ​ያም ንጹሕ መን​ገድ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም የተ​ቀ​ደሰ መን​ገድ ይባ​ላል፤ በዚ​ያም ንጹ​ሓን ያል​ሆኑ አያ​ል​ፉ​በ​ትም፤ ርኩስ መን​ገ​ድም በዚያ አይ​ኖ​ርም፤ የተ​በ​ተ​ኑ​ትም በእ​ርሱ ይሄ​ዳሉ፤ አይ​ሳ​ሳ​ቱ​ምም።


በውኑ በአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት መካ​ከል ያዘ​ንብ ዘንድ የሚ​ችል ይገ​ኛ​ልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰ​ጥና ሊያ​ጠ​ግብ ይች​ላ​ልን? አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ አን​ተን በተ​ስፋ እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድና የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ነገር ይን​ገ​ረን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ን​ገድ ላይ ቁሙ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ የቀ​ደ​መ​ች​ው​ንም መን​ገድ ጠይቁ፤ መል​ካ​ሚቱ መን​ገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ሂዱ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤” እነ​ርሱ ግን፥ “አን​ሄ​ድ​ባ​ትም” አሉ።


እና​ንተ የጽ​ዮን ልጆች ሆይ! በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጉ፤ ምግ​ብን በጽ​ድቅ ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ቀድ​ሞ​ውም የበ​ል​ጉ​ንና የመ​ከ​ሩን ዝናብ ያዘ​ን​ብ​ላ​ች​ኋ​ልና።


ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።


ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤


ደግሞ መል​ካ​ሙ​ንና ቅኑን መን​ገድ አሳ​ያ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ስለ እና​ንተ መጸ​ለ​ይ​ንና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማገ​ል​ገ​ልን በመ​ተው እር​ሱን እበ​ድል ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን አያ​ድ​ር​ግ​ብኝ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios