Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 22:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮቼ ጋር በመ​ር​ከብ ይሂዱ” አለው፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን አል​ወ​ደ​ደም።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 በዚያ ጊዜም የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ኢዮሣፍጥን “ሰዎቼ ከሰዎችህ ጋራ በመርከብ ይሂዱ” ሲል ጠይቆት ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ዕሺ አላለውም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

49 ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስን ዓይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኞች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ሐሳቡን አልተቀበለም።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

49 የአክዓብም ልጅ አካዝያስ ኢዮሣፍጥን “ባሪያዎቼ ከባሪያዎችህ ጋር በመርከብ ይሂዱ፤” አለው፤ ኢዮሣፍጥ ግን አልወደደም።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 22:49
8 Referências Cruzadas  

ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ ኢዮ​ራም ነገሠ።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር በኤ​ር​ትራ ባሕር ዳር በኤ​ላት አጠ​ገብ ባለ​ችው በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር መር​ከ​ቦ​ችን ሠራ።


ኪራ​ምም በእ​ነ​ዚያ መር​ከ​ቦች ከሰ​ሎ​ሞን አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር ባሕ​ሩን መቅ​ዘፍ የሚ​ያ​ውቁ መር​ከ​በ​ኞች አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ላከ።


ወደ አፌ​ርም ደረሱ፤ ከዚ​ያም አራት መቶ ሃያ መክ​ሊት ወርቅ ወሰዱ፤ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞ​ንም ይዘው አገቡ።


ከዚ​ህም በኋላ የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከአ​ካ​ዝ​ያስ ጋር ተባ​በረ፤ ይህም በደ​ልን የሠራ ነበር፦


የነ​ፍ​ሱ​ንም ዋጋ ለውጥ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios