Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 22:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የቀ​ረ​ውም የአ​ክ​ዓብ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ነገር ሁሉ፥ ከዝ​ሆን ጥር​ስም የሠ​ራው ቤት፥ የሠ​ራ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ሌላው በአክዓብ ዘመነ መንግሥት የተፈጸመውና ያደረገው ሁሉ፣ ቤተ መንግሥቱን መሥራቱና በዝኆን ጥርስ መለበጡ እንዲሁም የሠራቸው የምሽግ ከተሞች በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፥ ቤተ መንግሥቱን በዝሆን ጥርስ እንዴት አስጊጦ እንደ ሠራውና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ንጉሥ አክዓብ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ፥ ቤተ መንግሥቱን በዝሆን ጥርስ እንዴት አስጊጦ እንደ ሰራውና የሠራቸውም ከተሞች ሁኔታ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 የቀረውም የአክዓብ ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የሠራው ቤት፥ የሠራቸውም ከተሞች ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 22:39
16 Referências Cruzadas  

ንጉ​ሡም ደግሞ ከዝ​ሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠራ፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው።


ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራ​ዎ​ቹም ሁሉ፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥት ታሪክ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ነገር ግን በሸ​መ​ገለ ጊዜ እግ​ሮቹ ታመሙ።


የቀ​ረ​ውም የና​ባጥ ነገ​ርና ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የዘ​ምሪ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ዐመፅ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።


የቀ​ረ​ውም ዘን​በሪ ያደ​ረ​ገው ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ጭከና፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።


የቀ​ረ​ውም የባ​ኦስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሁሉ፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ ነው።


አክ​ዓ​ብም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


አካ​ዝ​ያስ ያደ​ረ​ገው የቀ​ረ​ውም ነገር እነሆ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል። በእ​ር​ሱም ፋንታ የአ​ክ​ዓብ ልጅ ወን​ድሙ ኢዮ​ራም ነገሠ።


የቀ​ረ​ውም የሴ​ሎም ነገር፥ የተ​ማ​ማ​ለ​ውም ዐመፅ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሓፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ፥ በም​ድር ያደ​ረ​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት እን​ድ​ታዩ ኑ።


የሮ​ድ​ያን ልጆ​ችም ነጋ​ዴ​ዎ​ችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደ​ስ​ያት ሰዎ​ችም የዝ​ኆን ጥርስ ይነ​ግ​ዱ​ልሽ ነበር፤ ከዚ​ያም የመጡ ሰዎች ዋጋ​ሽን ይሰ​ጡሽ ነበር።


ከባ​ሳን ኮም​ቦል መቅ​ዘ​ፊ​ያ​ሽን ሠር​ተ​ዋል፤ መቅ​ደ​ስ​ሽ​ንም በዝ​ኆን ጥርስ ሠሩ፤ ከኪ​ቲም ደሴ​ቶች ዛፍም ቤቶ​ች​ሽን ሠር​ተ​ዋል።


የክ​ረ​ም​ቱ​ንና የበ​ጋ​ዉን ቤት እመ​ታ​ለሁ፤ በዝ​ሆ​ንም ጥርስ የተ​ለ​በ​ጡት ቤቶች ይጠ​ፋሉ፤ ሌሎ​ችም ታላ​ላ​ቆች ቤቶች ይፈ​ር​ሳሉ” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios