Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ኤል​ሳ​ዕም በሬ​ዎ​ቹን ተወ፤ ኤል​ያ​ስ​ንም ተከ​ትሎ ሄደ፥ “አባ​ቴ​ንና እና​ቴን እስ​ማ​ቸው ዘንድ፥ እባ​ክህ ተወኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ እከ​ተ​ል​ሃ​ለሁ” አለው። እር​ሱም“ሂድና ተመ​ለስ፤ ምን አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ከዚያም ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ኤልያስን ተከትሎ እየሮጠ፣ “አባቴንና እናቴን ስሜ እንድሰናበታቸው ፍቀድልኝ፤ ከዚያም እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም መልሶ፣ “እኔ ምን ያደረግሁህ ነገር አለ? ልትመለስ ትችላለህ” አለው።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በሬዎቹንም ተወ፤ ከኤልያስም በኋላ ሮጦ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ፤” አለው። እርሱም “ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 19:20
8 Referências Cruzadas  

ወይስ ወን​ዶ​ቹ​ንና ሴቶ​ቹን ልጆ​ችን እስም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምን? አሁ​ንም ይህን እንደ አላ​ዋቂ አደ​ረ​ግህ።


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ “እነሆ፥ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?” አለው።


ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት።


እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ሁሉም እጅግ አለ​ቀሱ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አን​ገ​ቱን አቅ​ፈው ሳሙት።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios