Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 14:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የቀ​ረ​ውም የሮ​ብ​ዓም ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ ተጽ​ፎ​አል።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 የቀረው የሮብዓም አገዛዝ፣ ያደረገውም ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ንጉሥ ሮብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 የቀረውም የሮብዓም ነገር፥ ያደረገውም ሁሉ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 14:29
22 Referências Cruzadas  

የቀ​ረ​ውም የሰ​ሎ​ሞን ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ ጥበ​ቡም ሁሉ፥ እነሆ፥ በሰ​ሎ​ሞን የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዘወ​ትር ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሲገባ ዘበ​ኞች ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሰ​ውም በዘ​በ​ኞች ቤት ውስጥ ያኖ​ሩ​አ​ቸው ነበር።


የቀ​ረ​ውም የአሳ ነገር ሁሉ ብርቱ ሥራ​ዎ​ቹም ሁሉ፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥት ታሪክ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ነገር ግን በሸ​መ​ገለ ጊዜ እግ​ሮቹ ታመሙ።


በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምና በሮ​ብ​ዓም መካ​ከል በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ጠብ ነበረ።


የቀ​ረ​ውም የአ​ብያ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ እነሆ፥ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? በአ​ብ​ያና በኢ​ዮ​ር​ብ​አም መካ​ከል ሰልፍ ነበረ።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


ከአ​ባ​ቱም ከአሳ ዘመን የቀ​ረ​ውን ርኩስ ሥራ ከም​ድር አጠፋ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ተነ​ሥ​ተው ዐመ​ፁ​በት፥ ወደ ሲላ በሚ​ወ​ር​ደ​ውም መን​ገድ በመ​ሀሎ ቤት ኢዮ​አ​ስን ገደ​ሉት።


የቀ​ረ​ውም የአ​ሜ​ስ​ያስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የሴ​ሎም ነገር፥ የተ​ማ​ማ​ለ​ውም ዐመፅ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሓፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ታም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የዓ​ዛ​ር​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም አካዝ ያደ​ረ​ገው ነገር እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ነገር፥ ኀይ​ሉም ሁሉ፥ ኵሬ​ው​ንና መስ​ኖ​ውን እንደ ሠራ፥ ውኃ​ው​ንም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ዳ​መጣ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ታሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የም​ና​ሴም የቀ​ረው ነገ​ርና የሠ​ራው ሥራ ሁሉ፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ኀጢ​አት፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የአ​ሞ​ጽም የቀ​ረው ነገ​ርና የሠ​ራው ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ስ​ያስ ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​አ​ቄም ነገር፥ የሠ​ራ​ውም ሥራ ሁሉ፥ እነሆ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የተ​ረ​ፈ​ውም የኢ​ዮ​ራም ነገር ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የአ​ሜ​ስ​ያስ ነገ​ሮች፥ እነሆ፥ በይ​ሁ​ዳና በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios