Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሰው ተከ​ት​ሎት ሄደ፤ ከዛፍ በታ​ችም ተቀ​ምጦ አገ​ኘ​ውና፥ “ከይ​ሁዳ የመ​ጣህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እር​ሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እየጋለበ ያን የእግዚአብሔር ሰው ተከተለው። ከዚያም በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘውና፣ “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ሰው የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የባሉጥ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከይሁዳ የመጣው የእግዚአብሔር ነቢይ የሄደበትን መንገድ አቅጣጫ ይዞ ተከተለው፤ በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦም አገኘው። ሽማግሌውም “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ነቢይ አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት።

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከእግዚአብሔርም ሰው በኋላ ሄደ፤ በአድባርም ዛፍ በታች ተቀምጦ አገኘውና “ከይሁዳ የመጣህ የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” አለው። እርሱም “እኔ ነኝ፤” አለ።

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 13:14
9 Referências Cruzadas  

አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።


ልጆ​ቹ​ንም፥ “አህ​ያ​ዬን ጫኑ​ልኝ” አላ​ቸው፥ አህ​ያ​ው​ንም ጫኑ​ለት ተቀ​መ​ጠ​በ​ትም።


እር​ሱም፥ “ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና፥ እን​ጀ​ራም ብላ” አለው።


እር​ሱም አንድ ቀን የሚ​ያ​ህል መን​ገድ በም​ድረ በዳ ሄደ፤ መጥ​ቶም ከደ​ድሆ ዛፍ በታች ተቀ​መ​ጠና፦ ይበ​ቃ​ኛል፤ አሁ​ንም አቤቱ! እኔ ከአ​ባ​ቶቼ አል​በ​ል​ጥ​ምና ነፍ​ሴን ውሰድ” ብሎ እን​ዲ​ሞት ለመነ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ኔስ መብል የላ​ከ​ኝን የአ​ባ​ቴን ፈቃድ አደ​ርግ ዘንድ፥ ሥራ​ው​ንም እፈ​ጽም ዘንድ ነው።


በዚ​ያም የያ​ዕ​ቆብ የውኃ ጕድ​ጓድ ነበረ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ገድ በመ​ሄድ ደክሞ በዚያ ጕድ​ጓድ አጠ​ገብ ተቀ​መጠ፤ ጊዜ​ውም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር።


በድ​ካ​ምና በጥ​ረት፥ ብዙ ጊዜም ዕን​ቅ​ልፍ በማ​ጣት፥ በመ​ራ​ብና በመ​ጠ​ማት፥ አብ​ዝ​ቶም በመ​ጾም፥ በብ​ር​ድና በመ​ራ​ቆት ተቸ​ገ​ርሁ።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios