Biblia Todo Logo
A Bíblia On-line

- Anúncios -




1 ነገሥት 12:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ሳማያ እን​ዲህ ሲል መጣ።

Ver Capítulo Cópia de

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል፣ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ሆነው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን የጌታ ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማዕያ መጣ፥

Ver Capítulo Cópia de

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማዕያ መጣ፥

Ver Capítulo Cópia de

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሳማያ

Ver Capítulo Cópia de




1 ነገሥት 12:22
17 Referências Cruzadas  

እነ​ሆም፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከይ​ሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


በቤ​ቴ​ልም አንድ ሽማ​ግሌ ነቢይ ይኖር ነበር፤ ልጆ​ቹም ወደ እርሱ መጥ​ተው በዚ​ያች ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በቤ​ቴል ያደ​ረ​ገ​ውን ሥራ ሁሉ ነገ​ሩት፤ ደግ​ሞም ለን​ጉሡ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ሁሉ ለአ​ባ​ታ​ቸው ነገ​ሩት፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ተቈ​ጣ​ቸው።


እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው።


ሴቲ​ቱም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በአ​ፍህ እው​ነት እንደ ሆነ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ​ችው።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “በሚ​መ​ጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታ​ቀ​ፊ​ያ​ለሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም፥ “አይ​ደ​ለም ጌታዬ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አትዋ​ሻት” አለ​ችው።


ባል​ዋ​ንም ጠርታ፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ዘንድ በፍ​ጥ​ነት እሄ​ዳ​ለ​ሁና አንድ ሎሌና አንድ አህያ ላክ​ልኝ” አለ​ችው።


እን​ዲ​ሁም ሄደች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ወጣች። ኤል​ሳ​ዕም ያችን ሴት ወደ እርሱ ስት​መጣ ባያት ጊዜ ሎሌ​ውን ግያ​ዝን፥ “እነ​ኋት፥ ሱማ​ና​ዊት መጣች፤


ወደ ተራ​ራ​ውም ወደ ኤል​ሳዕ ደርሳ እግ​ሮ​ቹን ጨበ​ጠች፤ ግያ​ዝም ሊያ​ር​ቃት መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም፥ “ነፍ​ስዋ አዝ​ና​ለ​ችና ተዋት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያን ከእኔ ሰው​ሮ​ታል፤ አል​ነ​ገ​ረ​ኝ​ምም” አለ።


መጥ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነገ​ረ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሄደሽ ዘይ​ቱን ሽጭ ዕዳ​ሽ​ንም ክፈዪ፤ በተ​ረ​ፈ​ውም ዘይት የአ​ን​ቺ​ንና የል​ጆ​ች​ሽን ሰው​ነት አድኚ” አላት።


ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ልብ​ሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፥ “ልብ​ስ​ህን ለምን ቀደ​ድህ? ንዕ​ማን ወደ እኔ ይምጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ነቢይ እን​ዳለ ያው​ቃል” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ሰማያ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


የሮ​ብ​ዓ​ምም የፊ​ተ​ኛ​ውና የኋ​ለ​ኛው ነገር እነሆ፥ በነ​ቢዩ ሰማ​ያና በባለ ራእዩ በአዶ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን? ሮብ​ዓ​ምም ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ጋር በዘ​መኑ ሁሉ ይዋጋ ነበር።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት።


አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


Siga-nos em:

Anúncios


Anúncios